በጋምቤላ ክልል ከ150 ሺህ በላይ ለሚሆኑ ህፃናት የቤት ለቤት ፖሊዮ ክትባት እየተሰጠ ነው

በጋምቤላ ክልል ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች ለሆኑ ከ150 ሺህ በላይ ህፃናት የቤት ለቤት ፖሊዮ ክትባት እየተሰጠ ነው፡፡

የክትባት ፕሮግራሙ ከሚያዚያ 14 እስከ 17 ቀን 2011 ዓ.ም እንደሚካሄድ ነው የተገለጸው፡፡

ክትባቱ ጋምቤላ ከተማን ጨምሮ በ14 ወረዳዎችና በሰባት የስደተኛ ጣቢያዎች እየተሰጠ እንደሚገኝ የጋምቤላ ክልል ፕሬስ ሴክሬታሪያት ጽህፈት ቤት የህዝብ ግንኙነት አስተባባሪ አቶ ወንድምአገኝ በላይነህ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ዕድሜያቸው ከ5 ዓመት በታች የሆኑ 151 ሺህ 761 ህፃናት ክትባቱን እንደሚወስዱም ገልፀዋል፡፡

የአካባቢው ህብረተሰብም ልጆቹን በወቅቱ በማሰከተብ እንዲተባበር የክልሉ ጤና ጥበቃ ቢሮ ጥሪ ማስተላላፉን አቶ ወንድምአገኝ ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ብርሀኑ