ጦማር/ዜና

ቀዳማዊ ኃይለስላሴ

ቀዳማዊ ኃይለስላሴ በዲፕሎማሲያዊ ክህኖታቸዉ እና ከምእራብ አገሮች መሪዎች ጋራ በነበራቸዉ ቅርበት: የአሜሪካ ፕሬዘዳቶች በአፍሪካ መዲና በአገረ ኢትዮጰያ ብቅ ትልቅ ቢሉ ምንም አያስገርምም ነበር,
ይህ ሊሆን አልቻለም። እግዚአብሔር የፈቀደዉ አህጉሯን የመሰለ, በመምሰል ብቻ ሳይሆን በደሙ አፍሪካዊ በዜግነት አሜሪካዊ የሆነ ፕሬዘዳንት በምስራቅ አፍሪቃ በታላቋ የታሪክ ባለቤት ኢትዮጰያ እና በጎረቤት እና ለፕሬዘዳንቱ ከፊል ባለቤት በሆነቺዉ ኬንያ እንዲመጡ ሆነ።

በዚህ ታሪካዊ ጉብኝት ይህንን ለማለት ወደድን
ያባታቸዉን አገር እንደረገጡ ያስቀደሙት በግራ እህታቸዉን በቀኝ አያታቸዉን አስቀምጠዉ ከዘመዳዝማድ ጋራ እንጀራ መቁረስን የመረጡበት ምሽት አይረሴ ነበር
በስታዲዮሙ ያደረጉት ታሪካዊ ንግግራቸዉ እና ሌሎችም ክንዋኔዎች ቢኖሩም በጋዜጠኞች ስብሰባ ላይ ያገሩ ፕሬዘዳንት ኬንያታ ግብረሶዶማዉያንን በተመለከተ, “ይህ የናንተ ችግር ነዉ የአፍሪቃ አይደለም ብዙ ሊፈወሱ የሚፈለጉ ችግሮች አሉን ለዚህ ቦታ አንሰጠዉም” ያሉት, አገራቸዉን ብቻ ሳይሆን መላዉ አፍሪካን ያኮራ መልስ ነበርና እጅ ነስተናል

አዲስ አበባ ህዝቧ ብቻ ሳይሆን የነበረዉ በአፍሪካ ህብረት ስብሰባ ምክንያት አፍሪካዉያን ከነመሪዎቻቸዉ በመዲናችን ነበሩና ይህንን ጉብኝት ታሪካዊ እና ግለት እንዲኖረዉ አድርጎታል

በታላቁ ቤተመንግስት የእራት ግብዣ ላይ የሰዉን መጀመሪያነት በኢትዮጰያ ያረጋገጠችልንን ከእናት ሉሲ ጋራ መገናኘታቸዉ እና ትከሻቸዉን በስክስታ ወዝወዝ ያደረጉበት እና የቡናና የእጣኑ ምሽት ኢትዮጰያዊነትን አላብሶአቸዉ ነበር ።

በአፍሪካ ህብረት ታሪክ, ተቀማጭ የአሜሪካ መሪ ብቻ ሳይሆን, አለም ያላሰበችዉ የአሜሪካ ጥቁር ፕሬዘዳንት ከወድሞቻቸዉና ከእህቶቻቸዉ ጋራ በአባት ኔልሰን ማንዴላ ስም በተሰየመ አዳራሽ ጣሪያ ስር የታሪካዊ ንግግር ክስተት, መቼ ሊደገም ይችላል የሚለዉን ጥያቄ እንዳናስበዉ ያደርገናል።

በንግግራቸዉ ላይ ለሰዉ ልጅ እኩልነት, መብት እንዲሁም ክብር የሰጠው ትምህርታዊ መልእክት ለታሪክ የሚቀመጥ ነዉ። ከምንም በላይ ግን የስልጣን ዘመንን በተመለከተ ምነዉ ወድሞቼ ይህ አላስፈላጊ እና ሊገባኝ እማይችል ጉዳይ ነዉ, በተለይ ባለሃብት ሆናችሁ ማረፍን አለመፈለጋችሁ የሚገርም ነዉና እባካችሁ ስላጣንን ዉስን አድርጉት ያሉት ንግግር ከጆሮ እማይወጣ ነዉ።

ለአሜሪካ ቀረጥ ከፋዮች ወደ ስድስት ሚሊዮን ዶላር ያወጣዉ ይህ የሁለቱ ጎረቤታማቾች ጉብኝትን ሁለቱም አገሮች በሰላም ስለተወጡት ሊመሰገኑ ይገባል።

በመጨረሻ አንድ ነገር ልበል, በፈረንጆች አቆጣጠር በ1973 የኩባዉ መሪ “በኛ እና በአሜሪካ ሰላም ሊወርድ የሚችለዉ አሜሪካ ወደፊት ጥቁር ፕሬዘዳንት ሲኖራትና የካቶሊክ ፖፕ ከላቲን አሜሪካ ሲመረጥ ነዉ” ብለዉ ነበር። ይህንን ትንቢት ትላንት የአፍሪካዉ ህብረት ዋና ሃላፊ ዶክተር ዙማ ፕሬዘዳንት ኦባማን ሲያስተዋዉቁ አንስተዉት ነበር። የሚገርም ክስተት።

ቸር ይግጠመን!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *