መደበኛ ያልሆነ

ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡

/ / ዓብይ አህመድ የአውሮፓ ጉብኝታቸውን ጀመሩ፡፡

 

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠ/ሚ ዶ/ር ዐብይ አህመድ በአውሮፓ የሚያደርጉትን ይፋዊ የስራ ጉበኝት የጀመሩ ሲሆን በዛሬው እለት (ጥቅምት 19 ቀን 2011 ዓ.ም) ፈረንሳይ ገብተዋል።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ በፈረንሳይ ቆይታቸው ከሀገሪቱ ፕሬዚዳንት ኢማኑኤል ማክሮን ጋር ተገናኝተው በአጠቃላይ የሁለትዮሽና የጋራ አጀንዳ በሆኑ አካባቢያዊና አለምዓቀፋዊ ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ።

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት ጉብኝቱ የሁለቱን አገራት ግንኙነት ታሪካዊነትና ጥንካሬ የሚያሳይ ከመሆኑም በተጨማሪ ያለውን አጠቃላይ ትብብር ወደ ላቀ ደረጃ የሚያሳድግ ነው ተብሎ ይታመናል።

ዶ/ር አብይ በፈረንሳይ የሚያደርጉትን ጉብኝት እንዳጠናቀቁ በቀጥታ ወደ ጀርመን በርሊን በማምራት ማክሰኞ (ጥቅምት 20 ቀን 2011 ዓ.ም) ከጀርመን መራሂተ-መንግስት አንጌላ መርከልና ሌሎች የጀርመን ከፍተኛ ባለስልጣናት ጋር የሁለቱን አገራት ሁለንተናዊ ግንኙነት ወደ ላቀ ደረጃ ማሳደግ በሚቻልበት ሁኔታ ይወያያሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ከጀርመን የተመረጡ ግዙፍ ኩባንያዎች ጋርም ይወያያሉ።

ጠቅላይ ሚኒስትሩ ጉብኝቱን እያደረጉ የሚገኙት በሁለቱ አገሮች መሪዎች በቀረበላቸው ግብዣ መሰረት ነው።

የበርሊን ኦፊሴላዊ ውይይታቸውን እንዳጠናቀቁ ጠቅላይ ሚኒስትሩ ረቡዕ (ጥቅምት 21 ቀን 2011 ዓ.ም) ወደ ሌላኛዋ የጀርመን ከተማ ፍራንክፈርት በማምራት ከመላው አውሮፓ ከተውጣጡ ከ25 ሺ በላይ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ-ኢትዮጵያውያን ጋር “አንድ ሆነን እንነሳ ነገን በጋራ እንገንባ” በሚል መሪ ቃል አገርን በጋራ እንዴት እንገንባ በሚልና መንግስት ዳያስፖራውን እንዴት ይደግፍ በሚል ውይይት ያካሂዳሉ።

በአውሮፓ የዳያስፖራ ትረስት ፈንድ የሚቋቋምበት ሁኔታ ሃሳብ መለዋወጥም ከአጀንዳዎች መካከል አንዱ ነው ተብሎ ይጠበቃል።

 

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *