መደበኛ ያልሆነ

በኦሮሚያ ክልል በአንድ ሳምንት ውስጥ 79 የትራፊክ አደጋዎች ደረሱ፡፡

ከጥቅምት 19 እስከ ጥቅምት  25  ዓ.ም ድረስ በደረሰው የትራፊክ አደጋ የ14ሰዎች ህይወት ሲያልፍ በ9 ሠዎች ላይ ከባድ፣ 5 ሰዎች ላይ ደግሞ ቀላል የአካል ጉዳት እንዲሁም 51 የንብረት አደጋ ደርሷል፡፡

አደጋዎቹ በፍቼ ከተማ፣በጅማ፣ በምእራብ እና በምስራቅ ሀረርጌ ፣በምእራብ በደቡብ ምእራብ እና በሰሜን ሸዋ ፣በምእራብ አርሲ፣ምስራቅ ወለጋ እና ቡራዮ ከተማ የደረሱ ናቸው፡፡

የአደጋው ሁኔታ ካለፈው ሳምንት ጋር ሲነፃፀር የቀነሰ ሲሆን የአደጋዎቹ አብዛኛዎቹ ምክንያቶች ርቀትን ጠብቆ አለማሽከርከር መሆኑን የኦሮሚያ ክልል ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ባለሙያ ኮማንደር ደረጀ ፈጠነ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡

ሳምራዊት ስዩም

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *