መደበኛ ያልሆነ

የካናዳው ጠቅላይ ሚ/ር ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ የሥልክ ጥሪ አደረጉ፡፡

የካናዳው ጠቅላይ ሚ/ር ለኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ ዓህመድ የሥልክ ጥሪ አደረጉ፡፡
የካናዳው ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ከኢ.ፌ.ዲ.ሪ. ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር ዓብይ አህመድ ጋር በስልክ ባደረጉት ውይይት ኢትዮጵያውያን ሴቶች በቁልፍ አመራር ቦታዎች እንዲሳተፉ መደረጉን እንደሚያደንቁ ገልጸውላቸዋል፡፡

የውጭ ጉዳይሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት ጀስቲን ትሩዶ በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ በሙሉ ልብ ለመደገፍ መንግስታቸው ዝግጁ መሆኑንም ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የመጣውን ለውጥ ተከትሎ አገሪቱ ለቀጠናው ሰላም እና ደህንነት እየተጫወተች ያለውን ሚናም አድንቀዋል፡፡

ጠቅላይ ሚኒስትር ጀስቲን ትሩዶ ኢትዮጵያን በቅርቡ ለመጎብኘት ያላቸውን ፍላጎት ለጠቅላይ ሚኒስትር በስልክ ውይይታቸው ወቅት አንስተዋል::

በቅርቡ የኢትዮጵያን የወጭ ንግድ ዘርፍ ለማጠናከር እና የኢንቨስትመንት ፍሰቱ እንዲጨምር ለማድረግ በሁለቱ ወገኖች ስምምነት ላይ መደረሱ ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *