የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ የኤርትራና የሶማሊያ ፕሬዝዳንቶች የአማራ ክልልን እንዲጎብኙ በይፋ መጋበዛቸውን ተከትሎ የኤርትራው ፕሬዚዳንት ኢሳያስ አፈወርቂና የሶማሊያው ፕሬዚዳንት መሀመድ አብዱላሂ ዛሬ (ጥቅምት 30 ቀን 2011 ዓ.ም) አማራ ክልል ገብተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት ጠቅላይ ሚኒስትር አብይ አህመድና ምክትላቸው አቶ ደመቀ መኮንን እንዲሁም የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ከክልሉ ከፍተኛ አመራሮች ጋር በመሆን ፕሬዝዳንት ኢሳያስ አፈወርቂንና ፕሬዝዳንት መሀመድ አብዱላሂን በጎንደር ተቀብለዋቸዋል።
ጉብኝቱ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ በአፍሪካ ቀንድ ሰላምና ልማት ላይ አዎንታዊ ተፅእኖ ለመፍጠር የጀመሩት መሪ እንቅስቃሴ አካልና በመስከረም 2011 በኤርትራ አስመራ የተካሄደው የሶስትዮሽ ምክክር ተከታይ ሲሆን በጎንደርና ባህር ዳር የሚገኙ የልማት እንቅስቃሴዎችን መጎብኘትን እንደሚያካትት ታውቋል።