መደበኛ ያልሆነ

የአፍሪካ ልማት ባንክ ለኢትዮጵያ የገንዘብ እርዳታ አጸደቀ

የአፍሪካ ልማት ባንክ የ123 ሚሊዬን የአሜሪካ ዶላር እርዳታ ለኢትዮጵያ ለመስጠት አጽድቋል፡፡

ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት ገንዘቡ ለያዝነው እና ለሚቀጥለው ዓመት ለኢትዮጵያ መሰረታዊ የአገልግሎት ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም የሚውል ነው፡፡

ድጋፉ የሁለተኛውን የኢትዮጵያ መንግስት እድገት እና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ አካል የሆነውን የሰው ሃብት ልማት እና የቴክኖሎጅ አቅም ግንባታን ለማፋጠን እና ዘላቂ ለማድረግ ያግዛል፡፡

ድርጅቱ፣ ድጋፉን የሚያደርገው ኢትዮጵያ በሰው ሃብት ልማት ከፍተኛ መሻሻል ማሳየቷን በተለይም የህጻናት ሞትን መቀነሷን እና የገጠር ውሃ አቅርቦትን ከፍ ማድረግ መቻሏን ከግምት በማስገባት ነው፡፡

የመሰረታዊ አገልግሎት ትራንስፎርሜሽን ፕሮግራም፣ የአፍሪካ ልማት ፈንድ እና የኢትዮጵያ መንግስት ዓለም ባንክን ከመሰሉ የልማት አጋሮች ጋር በቅንጅት የተዘጋጀ ነው፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *