መደበኛ ያልሆነ

ዮኔስኮ የዓለም የፕሬስ ቀን በኢትዮጵያ እንዲከበር ወሰነ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዴኤታ ዶ/ር ማርቆስ ተክሌ ቢኢትዮጵያ የዮኔስኮ ተዋካይ ኤልሳ ሳንታና አልፎንሶ ጋር በጽ/ቤታቸው ተወያይተዋል፡፡

ኃላፊዋ ዓለም ዓቀፍ የፕሬስ ቀን በመጪው ግንቦት 2011 ዓ.ም በኢትዮጵያ እንዲከበር ዮኔስኮ መወሰኑን ገልፀው ኢትዮጵያ የሚድያ ምህዳሩን ለማስፋት የምታደርገውን ዕርምጃ አድንቀዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት ዮኔስኮ በኢትዮጵያ የሚካሄደውን የማሻሻያ እርምጃ ለመደገፍ ፅኑ ፍላጎት አንዳለውም ገልፀዋል፡፡

ዶ/ር ማርቆስ በበኩላቸው ዓለም አቀፍ የፕሬስ ቀን በኢትዮጵያ እንዲከበር ዮኔስኮ አገራችንን በመምረጡ አመስግነዋል፡፡
ዮኔስኮ በኢትዮጵያ የቅርስ ጥበቃ ለሚያደርገው ድጋፍ ሚኒስትር ዴኤታው አድነቆታቸውን ገልፀዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *