መደበኛ ያልሆነ

አና ጎሜዝ የኢትዮጵያን የለውጥ ሂደት ደገፉ

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት በቦልቴክና ቤኒሉክስ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ  ቋሚ መልዕክተኛና ባለሙሉ ስልጣን አባሳደር ግሩም አባይ ሀገራት የአውሮፓ ፓርላማ አባል ከሆኑት አና ጎሜዝ ጋር ተነጋግረዋል፡፡

አምባሳደር ግሩም በኢትዮጵያ እየተካሄደ  ስላለው ተቋማዊ ለውጥ፣ ሙስናን ለመዋጋት እየተደረገ ስላለው ትግል እንዲሁም በተለያዩ አገራዊ እና አካባቢያዊ ጉዳዮች ላይ  ማብራሪያ ሰጥተዋቸዋል፡፡

አና ጎሜዝ በበኩላቸው በኢትዮጵያ እየተካሄደ ያለውን የለውጥ ሂደት በቅርበት እንደሚከታተሉት እና ለጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ ጥረቶች አድናቆት እንዳላቸው ተናግረዋል፡፡

አና ጎሜዝ በ1997 ዓ.ም በኢትዮጵያ የተካሄደውን አጠቃላይ ምርጫ የታዘበውን የአውሮፓ ህብረት ቡድን መምራታቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *