መደበኛ ያልሆነ

በኢንደስትሪ ተቋማት ላይ ለሚደርሰው የእሳት አደጋ የቦታ ጥበት ቀዳሚ መንስኤ ነው ተባለ፡ ፡

በአዲስ አበባ በሚገ ኙ የኢንደስትሪ ተቋማት ላይ ከሚመመዘገ ቡ የእሳት አደጋዎች አብዛኞቹ
የሚደርሱት በቦታ ጥበት እና የስራ መሳሪያዎችን በአግባቡ ባለማስቀመጥ እንደሆነ የእሳት
እና ድንገ ተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን ባደረገ ው የዳሰሳ ጥናት
አመላክቷል፡ ፡
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በአደጋ ተጋላጭነ ት ዙሪያ፤ በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ ባካሄደው
ጥናት ለየሁት እንዳለው፤ የግንዛቤ ዕጥረት፤ ከቦታ ጥበት ጋር ተያይዞ ተረፈ ምርቶችን
በአግባቡ አለማስወገ ድ እና የኤሌክትሪክ ምርቶችን በአግባቡ አለመዘርጋት፤ ለአደጋ ምክንያት
ናቸው፡ ፡
ስለሆነ ም፤ እንዲህ ባለው ምክንያት የሚደርሰውን አደጋ ለመቀነ ስ እና ለመከላከል፤ የእሳት
እና ድንገ ተኛ አደጋዎች መከላከል እና መቆጣጠር ባለስልጣን፤ ግንዛቤ የመፍጠር እና
አስገ ዳጅነ ት ያላቸውን መመሪያዎች ስራ ለይ የማዋል ተግባር በቀጣዩ 1 ወር ጊዜ ውስጥ
እንደሚጀምር፤ የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ኮማንደር አህመድ መሀመድ ለብስራት ሬዲዮ
ተናግረዋል፡ ፡
በአዲስ አበባ ከሚገ ኙ ክ/ከተሞች በአደጋ ተጋላጭነ ት ከአቃቂ ክ/ከተማ በመቀጠል
በ2ተኝነ ት ደረጃ ላይ የሚገ ኘው ንፋስ-ስልክ ላፍቶ ክ/ከተማ 1ሺህ 500 የኢንደስትሪ
ተቋማት ይገ ኛሉ፡ ፡
ሄኖክ አለማየሁ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *