መደበኛ ያልሆነ

1300 ግራም አደገኛ የኮኬይን ዕጾችን በሆዱ ውስጥ ይዞ የተገኘው ተከሳሽ በጽኑ እስራት ተቀጣ

ናይጄሪያዊ ዜግነት ያለው ተከሳሽ ሚስተር ኢማኑኤል በፈፀመዉ የተከለከሉ ዕጾችን ማዘዋወር ወንጀል ክስ
ቀርቦበታል፡ ፡
የክስ መዝገ ቡ እንደሚያትተው ተከሳሽ የወንጅል ህግ አንቀጽ 525/1/ለ/ ስር የተመለከተውን በመተላለፍ
ልዩ ፍቃድ ሳይኖረዉ መስከረም 6 ቀን 2011 ዓ.ም ከብራዚል ሳኦፖሎ ወደ ናይጀሪያ ሌጎ ስ ለመሄድ
በመጓዝ ላይ እያለ በቦሌ አየር መንገ ድ በቁጥጥር ስር መዋሉን በጠቅላይ አቃቤ ህግ የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች
ዳይሬክተር አቶ ዝናቡ ቱኑ በተለይም ለብስራት ሬዲዮ ተናግረዋል፡ ፡
በጊዜዊ ማቆያ ቦታ በሆዱ ውስጥ ሰላሳ አምስት ጥቅል የኮኬይን ዕፅ የወጣ ሲሆን በፌዴራል ፖሊስ በምርመራ
ላይ እያለ ቀሪ ሰላሳ ሶስት ፍሬ ከሆዱ የወጣ በመሆኑ ተከሳሽ በአጠቃላይ ስልሳ ስምንት ጥቅል ፍሬ ወይም
አንድ ሺህ ሶስት መቶ ግራም ኮኬይን የተባለ አደገ ኛ ዕፅ በሆዱ ይዞ የተገ ኘ በመሆኑ መርዛማ ዕፆችን ይዞ
በመገ ኘትና በማዘዋወር ወንጅል ተከሶ ፍርድ ቤት ቀርቧል፡ ፡
ተከሳሹም ያለምንም መቃወሚያ ድርጊቱን ፈፅሜለሁ ጥፋተኛ ነ ኝ አባቴ የሞተ በመሆኑ ቤተሰቦችን ለመርዳት
ገ ንዘብ ለማግኘት ስል ድርጊቱን ፈጽሜያለሁ በማለት ተናግሯል፡ ፡
ዐቃቤ ሕግም ተከሳሹ የወንጀል ድርጊቱን ፈፅሜለሁ በማለቱ ሌላ ማስረጃ መሰማት ሳያስፈልግ የጥፋተኝነ ት
ውሳኔ እንዲሰጥ በማለት በችሎቱ በጠየቀው መሰረት የፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ 8ኛ ወንጀል
ችሎት ህዳር 13 ቀን 2011 ዓ.ም በዋለዉ ችሎት በ7 አመት ጽኑ እስራት እና በ7 ሺህ ብር የገንዘብ
መቀጮ አንዲቀጣ ሲል መወሰኑን አቶ ዝናቡ ጨምረው ነ ግረውናል፡ ፡
ፍሬህይወት ታደሰ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *