መደበኛ ያልሆነ

በሳምንቱ መጨረሻ ሁለት ቀናት በደረሱ የተለያዩ አደጋዎች 5 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

ከአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን ባገኘነው መረጃ መሰረት ቅዳሜ ዕለት በንፋስ ስልክ ወረዳ 1 አንዲት የ25 አመት ሴት ባልታወቀ ምክንያት ወንዝ ውስጥ ገብታ ህይወቷ አልፏል፡፡

በዛው እለት በየካ ክፍለ ከተማ ወረዳ 1 ወንድራድ ትምህርት ቤት አካባቢ አዲስ የተወለደ ጨቅላ ህፃን በመፀዳጃ ቤት ውስጥ ተጥሎ ሞቶ መገኘቱ ታውቋል፡፡

እሁድ እለት ደግሞ በአዲስ ከተማ ወረዳ 8 አማኑኤል ሆስፒታል ግቢ ውስጥ እድሜው 28 አመት የሆነ የአእምሮ ታማሚ ውሀ በተሞላ የውሀ ማጠራቀሚያ ታንከር ውስጥ ገብቶ ህይወቱ አልፏል፡፡

በሌላ በኩል በጉለሌ ወረዳ 2 ጀርመን ስኩል አካባቢ ምሽት 2፡25 ላይ መንገድ ዳር ተቆፍሮ ሳይዘጋ በቀረ  ጉድጓድ ውስጥ የ 45 ዓመት ሰው ሳይታሰብ ገብቶ ህይወቱ ማለፉ ተሰምቷል፡፡
እንደዚሁም በኮልፌ ቀራንዮ ወረዳ 2 ለካባ ተብሎ ተቆፍሮ በተተወ ጉድጓድ ውስጥ የ27 አመት ወጣት ገብቶ ህይወቱ ማለፉ ታውቋል፡፡

የአዲስ አበባ እሳትና ድንገተኛ አደጋ መከላከልና መቆጣጠር ባለስልጣን የህዘብ ግንኙነት ባለሙያ አቶ ንጋቱ ማሞ ለብስራት ሬድዮ እንደተናገሩት ህይወታቸውን ያጡት የአደጋው ሰለባዎች አስክሬናቸው በሙያተኞች ወጥቶ ለተጨማሪ ምርመራ ለፖሊስ አስረክበዋል፡፡

 

 

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *