መደበኛ ያልሆነ

ኢትዮጵያ ‘በአፍሪካ የሰላም ጎዞ’ ላይ ተሳተፈች

በአፍሪካ ሰላም፣ አካባበያዊ ልማትና ብልፅግና ላይ አጋርነትን ለማሳየት በየአመቱ በሚካሄደው በጂቡቲ አርታ የእግር ጉዞ ላይ ኢትዮጵያ ተሳትፋለች፡፡

“የአፍሪካ የሰላም ጉዞ” በተሰኘ መሪ ቃል ለ12ኛ ጊዜ በአርታ በተካሄደው የእግር ጉዞ የጂቡቲን ጨምሮ በርካታ የአፍሪካ እና የተለያዩ የዓለም አገራት ተሳትፈውበታል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መግለጫ መሰረት 15 ኪሎ ሜትር በሸፈነው የእግር ጉዞ ኢትዮጵያ ሰንደቅ ዓላማዋን ከፍ በማድረግ የእግር ጉዞው ድምቀት ሆና ውላለች።

በጂቡቲ የኢ.ፌ.ዲ.ሪ ኤምባሲ ሰራተኞች፣ በጂቡቲ የሚኖሩ ኢትዮጵያውያንና ትውልደ ኢትዮጵያውያን እንዲሁም የኢትዮጵያ ወዳጆች ሰንደቅ ዓላማዋን አንግበው በእግር ጉዞው ተሳታፊ ሆነዋል፡፡

ኢትዮጵያ በአፍሪካ ሰላምና ልማት ላይ ቁልፍ ሚና ያላት ሲሆን በተ.መ.ድ የዓለም የሰላም አስከባሪ ሃይሎች ዜጎቿን በማሰለፍ የመጀመሪያ ደረጃ መያዟም ይታወቋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *