መደበኛ ያልሆነ

የኦስቲሪያው ቻንስለር ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ

የኦስትሪያው ቻንስለር እና የወቅቱ የአውሮፓ ህብረት ምክር ቤት ሊቀመንበር ሳባስቲያን ኩርዝ (Sebastian Kurz) የፊታችን  ሃሙስ ኢትዮጵያን ይጎበኛሉ፡፡

በ ኢ.ፌ.ዲ.ሪ ጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ በተደረገላቸው ግብዣ መሰረት ኢትዮጵያን የሚጎበኙት ቻንስለሩ በሁለትዮሽ እና በቀጠናው ጉዳዮች ላይ ይወያያሉ፡፡

እ.ኤ.አ. ከዲሴምበር 17 እስከ 18/2018 በኦስትሪያ ቬይና በሚካሄደው የአፍሪካ እና የአውሮፓ የመሪዎች ጉባኤ ላይ በሚኖሩ ጉዳዮች ላይም ይመክራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡
ኦስትሪያ በኢትዮጵያ የኃይል፣ የጤና እና የግብርና ዘርፎች ላይ የልማት ትብብር ታደርጋለች፡፡

ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት የሁለቱ አገራት ግንኙነት ከአንድ ምዕተ ዓመት በላይ ያስቆጠረ ነው፡፡

በ19ኛው መቶ ክፍለ ዘመን በኦስትሪያ ንግስት ማሪያ ትሬዛ ስም ይጠራ የነበረውን ገንዘብ አገራችን ለመገበያያነት ትጠቀምበት እንደነበር ይታወቃል፡፡

ቻንስለር ሳባስቲያን ኩርዝ ከሁለት አመት በፊት የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር በነበሩበት ወቅት በአገራችን ጉብኝት ማድረጋቸው ይታወሳል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *