መደበኛ ያልሆነ

በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ መኪኖች ማምረት ሊቻል ነው

ከመኪና የሚወጣውን ጭስ ለማስቀረት በኤሌክትሪክ እና በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ መኪኖችን ለማምረት ድራይቭ ቴክ ከተሰኘው የኮሪያው ኩባንያ በኢትዮጵያ በታዳሽ ሀይል በሚሰሩ መኪኖች ለመገጣጠም የሚያስችለውን የገበያ ጥናት አጠናቁዋል ሲሉ በኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የህዝብ ግንኑነት ባለሙያ አቶ ገብረጊዮርጊስ አሰፋ በተለይም ለብስራት ራዲዮ ተናግረዋል፡፡

ከአየር ንብረት ለውጥ ጋር በተያያዘ የአረጓዴ ኢኮኖሚን ለመገንባት በሚደርገው ጥረት የአለም ሀገራት የተለያዩ አማራጮችን እየፈለጉ ይገኛል፡፡  ከዚህም ውሰጥ አንዱ  ከመኪና የሚወጣውን  ጭስ ለማስቀረት በኤሌክትሪክ እና በፀሀይ ሀይል የሚሰሩ መኪኖችን ማምረት ነው፡፡

በዚህ ዘርፍ የተሰማራው ድራይቨ ቴክ የተሰኘው የኮሪያ ኩባኒያ የኤሌክትሪክ ምርቶችን ለማምርት እና በታዳሽ ሀይል የሚሰሩ መኪኖችን መገጣጠም በሚቻልበት ሁኔታ የኩባኒያው ስራ አስኪያጅ ዩን ዮኝግ ቼይ ከኢኖቨሽን እና ቴክኖሎጅ ሚንስቴር ሚንስትር ዴኤታ እቶ ጀማል በከር ጋር መክረዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ኢትዮጵያ የያዘችውን የአረንጓዴ ኢኮኖሚ ልማት የሚደግፍ በመሆኑ መንግስት አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርግ አርጋግጠውላቸዋል፡፡

 

ሳምራዊት ብርሀኑ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *