አምባሳደሮች፣ የተለያዩ ሀገራት ዲፕሎማቶች የአየር መንገዱ ማኔጅመንት ሰራተኞችና አመራሮች በተገኙበት የአየር መንገዱ ዋና ስራ አስፈጻሚ አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም በረራውን አስጀምረዋል።
አቶ ተወልደ ገ/ማሪያም ባደረጉት ንግግር በረራው መጀመሩ በቀጣይ በሁለቱ አህጉሮች መካከል ያለውን የንግድ፣ የቱሪዝም እና የኢቨስትመንት ግንኙነት እንደሚያሳድገው አስረድተዋል።
በፕሮግራሙ ላይ የተገኙት በውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ወይንሸት ታደሰ አዲሱ በረራ የኢትዮ-ሩሲያን ግንኙነት እንደሚያጠናክረው ገልጸዋል።
ኢትዮጵያና ሩሲያ ዲፕሎማቲክ ግንኙነታቸውን ከ 120 ዓመት በፊት የጀመሩ ሲሆን፣ግንኙነቱ ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መጥቷል፡፡
ብስራት ሬድዮ ከውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት በተላከለት መረጃ መሰረት፡- የኢትዮጵያ አየር መንገድ በሰባ ዓመት የአገልግሎት ዕድሜው በአህጉሪቱ ተመራጭ አየር መንገድ እንዲሆን አስችሎታል።
ስምኦን ደረጄ