መደበኛ ያልሆነ

የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰን በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋል፡፡

የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት ሬድዮ በላከው መረጃ መሰረት፡- ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ የኦሮሞ ጥናትን መሰረት የጣሉ ብቻ ሳይሆን በገዳ ስርዓት ለማጣቀሻ የበቁ አያሌ መፅሀፍቶችን የፃፉና ጥናቶችን ያደረጉ ናቸው፡፡

 

እነዚህ የአዕምሮ ውጤቶቻቸው ገዳ በዮኒስኮ እንዲመዘገብ ያስቻሉት ምሁር ዛበሬው እለት  የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ዶ/ር ወርቅነህ ገበየሁ በጽ/ቤታቸው ተቀብለዋቸዋል፡፡

 

እኚህ የገዳ ጥናት አባት የሆኑት ፕሮፌሰር አስምሮም ለገሰ ኤርትራዊ ይሁኑ እንጂ ልባቸውም ቀልባቸውም ከቦረና ኦሮሞዎች ጋር እንደሆነ ለዶ/ር ወርቅነህ ነግረዋቸዋል፡፡

 

በኦሮሞ ሙገሳ ስርዓት ኦሮሞነትን ያገኙት ፕሮፌሰር አስምሮም ከቦረና ኦሮሞዎች ጋር የተሳሰሩት ከ 50 ዓመት በፊት በቦረና አባገዳ ጄልቤሳ ሊበን አማካኝነት እንደሆነ በውይይቱ ወቅት አስታውሰው ፕሮፌሰር አስምሮም የአባገዳው ባለቤቶች የነበሩት ሙሴሌ እና ቱሪ በአጠቃላይ ቦረናዎች እኔን ብቻ ሳይሆን የጥናት ንብረቴን ሳይቀር ይንከባከቡ ነበር ብለዋል፡፡

 

የቦረና ህዝብ ባህል መዋሸት፣ መስረቅ፣ እና መግደልን ነውር ያደረገ ነው ያሉት ተመራማሪው ህብረተሰቡ ስለ ገዳ የበለጠ ዕውቀት እንዲኖረው በሌሎች ቋንቋዎች የተፃፉትንም መተርጎም ይገባል ብለዋል፡፡

ዶ/ር ወርቅነህ በበኩላቸው ፕሮፌሰር አስምሮም ገዳን ለዓለም በማስተዋወቅ ላደረጉት ነገር እናመሰግናለን ብለዋል፡፡
በኤርትራ እና የኦሮም ህዝብ መሀከል ፕሮፌሰሩ ድልድይ መሆናቸውን ገልፀው በቀጣይ ለጥናቶቻቸው በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስፈፃሚነት ድጋፍ ይደርጋል ብለዋል፡፡

 

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *