መደበኛ ያልሆነ

ኢትዮጵያን በወጭ ንግድ እና በኢንቨስትመንት ቀዳሚ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ ነው፡፡

ኢትዮጵያን በወጭ ንግድ እና በኢንቨስትመንት መስኮች ቀዳሚ ተደራሽ ለማድረግ እየተሰራ መሆኑን የኢ.ፌ.ዲ.ሪ የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር አስታውቋል።
በውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር የኢኮኖሚ ዲፕሎማሲ ቋሚ ተጠሪ አምባሳደር ደዋኖ ከድር መገኛቸውን አዲስ አበባ ካደረጉ ሚሲዮኖች ጋር በኢትዮጵያ ባሉ የኢንቨስትመንት እድሎች ዙሪያ ትናንት በጽህፈት ቤታቸው ተወያይተዋል።
የውጭ ጉዳይ ሚንስቴር ቃል አቀባይ ፅ/ቤት ለብስራት በላከው መግለጫ መሰረት አምባሳደር ደዋኖ በዚሁ ጊዜ፣ኢትዮጵያ የብዙ ሀገራት የንግድ እና የኢንቨስትመንት መዳረሻ መሆኗን አመላክተዋል፡፡
በርካታ ሀገራት መዋዕለ ነዋያቸውን በማፍሰስ በሀገሪቱ እድገት፣ በስራ ፈጠራ እና በቴክኖሎጂ ሽግግር ላይ ከፍተኛ አስተዋጽኦ እያደረጉ መሆናቸውንም ገልጸዋል።
ኢትዮጵያ ከፍተኛ የንግድና ኢንቨስትመንነት እምቅ አቅም እንዳላት ቋሚ ተጠሪው አስረድተው በዘርፉ የሚሰተዋሉ የአሰራር ክፍተቶች እና ቅሬታዎችን ለመፍታት እና ተጠቃሚ ለመሆን ከባለድርሻ አካላት ጋር በመሆን የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር እንደሚሰራ ገልጸዋል።

ስምኦን ደረጄ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *