ዜጎች በጎዳና ተዳዳሪነት እና በጎዳና ላይ የወሲብ ንግድ የሚሰማሩበት አስገዳጅ ሁኔታዎች ቢኖሩም ያሉትን ሌሎች አማራጮች ከመጠቀም ይልቅ እንደ ብቸኛ አማራጭ የሚወሰድበት ሁኔታዎች ይታያሉ፡፡
በዚህም በከተማዋ የጎዳና ተዳዳሪነትና የጎዳና ላይ የወሲብ ንግድ የሀገሪቱን እድገት በሚንፃረር መልኩ ተበራክቱዋል ሲሉ በአዲስ አበባ ሰራተኛና ማህበራዊ ጉዳይ ቢሮ የማህበራዊ ጎዳይ ሀላፊ ዳይሬክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ይድነቃቸው ሀይሉ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
የወጣውን ደንብ በተመለከተ መስራት የማይችሉትን በማህበር ለማቋቋም እየተሰራ እንደሆነ ተገልጿል፡፡
በተከለከሉ ጎዳናዎችና ቦታዎች ላይ ጎዳና ተዳዳሪነትን ፣ልመናንና በጎዳና ላይ የወሲብ ንግድን ለመከላከል የወጣውን ረቂቅ አዋጅ በተመለከተ ህብረተሰቡ እንዲሁም የሀይማኖት ተቋማት ከመንግስት ጎን መቆም እንዳለባቸው አቶ ይድነቃቸው ጨምረው ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል፡፡
ሳምራዊት ብርሀኑ