ወረርሽኙ በዲሞክራቲክ ኮንጎ ጎማ ከተማ በቅርቡ መቀስቀሱ ይታወቃል። በሽታው የዓለም ስጋት ነው ሲል የዓለም የጤና ድርጅት አስታውቋል።
የኢትዮጵያ ህብረተሰብ ጤና ኢንስቲትዩትም በሽታው ወደ ሀገር ውስጥ እንዳይገባ አስፈላጊውን ክትትል እያደረገ ይገኛል ሲሉ የኢስቲትዩቱ ም/ዋና/ዳይሬክተር ዶ/ር በየነ ሞገስ ለብስራት ተናግረዋል።
በተለይም የኢትዮጵያ አየር መንገድ ወደ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በሳምንት 25 በረራዎችን ማድረጉ ጉዳዩን አሳሳቢ ያደርገዋል።
ስለሆነም ወረርሽኙ ከተቀሰቀሰበት ስፍራ ወደ ኢትዮጵያ ለሚገቡ ተጓዞች የመለያ ስፍራዎች የተዘጋጁ ሲሆን ከ 2 እስከ 21 ቀናት ያህል ተገቢው ክትትልና ቁጥጥር እየተከናወነ ይገኛል።
በሽታው በቀላሉ የሚሰራጭ በመሆኑ 2000 ለሚሆኑ ባለሙያዎች ስልጠና ተሰጥቷል።
ከአየር ትራንስፓርት በተጨማሪም በተለያዩ ኬላዎች ላይ ቁጥጥር እየተደረገ ይገኛል።
ሚኪያስ ፀጋዬ