መደበኛ ያልሆነ

ዋልያዎቹ ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ከሌሴቶ ጋር ለሚያድረጉት ጨዋታ 24 ተጫዋቾች ተጠሩ።

የኢትዮጵያ ብሄራዊ ቡድን ለ2022 የኳታር የዓለም ዋንጫ ቅድመ ማጣሪያ ከሌሴቶ ጋር ለሚያድርገው ጨዋታ 24 ተጫዋቾች ተጠሩ፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን ከሌሴቶ ብሔራዊ ቡድን ጋር ነሐሴ 29 እና ጳጉሜ 3 በደርሶ መልስ ለሚያደርገው ጨዋታ የብሄራዊ ቡድኑ አሰልጣኝ አብርሃም መብራቱ ለ24 ተጫዋቾች ጥሪ አድርገዋል፡፡

ከ24ቱ ተጫዋቾች በተጨማሪ በኖርዌይ አንደኛ ዲቪዚዮን የሚጫወቱት ሁለት ተጫዋቾች ማለትም ስትሮምጎድሴት እግር ኳስ ክለብ በግብ ጠባቂነት የሚጫወተው ዳንኤል ንጉሴ፣ በሳርፕስበርግ እግር ኳስ ክለብ የአማካይ አጥቂ በመሆን ሚጫወተው አሚር አስካር እንዲሁም በጀርመን ሁለተኛ ዲቪዚዮን በሚገኝ ክለብ በተከላካይ ስፍራ የሚጫወተው ካሊድ ሙሉጌታ በአሰልጣኝ አብርሃም ጥሪ ተደርጎላቸዋል፡፡

ጥሪ የተደረገላቸው ተጫዋቾችም፦

1 ጀማል ጣሰው – ግብ ጠባቂ – ፋሲል ከነማ

2 ምንተስኖት አሎ – ግብ ጠባቂ- ባህር ዳር ከተማ

3 ለዓለም ብርሃኑ -ግብ ጠባቂ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

4 አስቻለው ታመነ – ተከላካይ – ቅዱስ ጊዮርጊስ

5 ያሬድ ባዬ -ተከላካይ – ፋሲል ከነማ

6 አንተነህ ተስፋዬ – ተከላካይ – ድሬዳዋ ከተማ

7 ረመዳን የሱፍ – ተከላካይ – ስሁል ሽረ

8 አምሳሉ ጥላሁን – ተከላካይ – ፋሲል ከነማ

9 አህመድ ረሽድ – ተከላካይ – ኢትዮጵያ ቡና

10 ደስታ ደሙ – ተከላካይ – ወልዋሎ አዲግራት ዩንቨርሲቲ

11 ዮናስ በርታ – ተከላካይ – ደቡብ ፖሊስ

12 ጋቶች ፓኖም – አማካኝ – አልጉዋና

13 አማኑኤል ዮሃንስ – አማካኝ – ኢትዮጵያ ቡና

14 ከነዓን ማርክነህ – አማከኝ – አዳማ ከተማ

15 ሀይደር ሸረፋ – አማካኝ – መቐለ 70 አንድርታ

16 ሽመልስ በቀለ – አማካኝ -አልመካሳ

17 ታፈሰ ሰለሞን – አማካኝ – ሐዋሳ ከተማ

18 ሱራፌል ደኛቸው – አማካኝ – ፋሲል ከነማ

19 አማኑኤል ገ/ሚካኤል -አጥቂ – መቐለ 70 እንድርታ

20 ዑመድ ኡክሪ – አጥቂ – አልሱሙማ

21 ቢኒያም በላይ – አጥቂ – ሱሪያንስ

22 አዲስ ግደይ – አጥቂ – ሲዳማ ቡና

23 ሙጅብ ቃሲም – አጥቂ – ፋሲል ከነማ

24 መስፍን ታፈሠ – አጥቂ – ሐዋሳ ከተማ

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *