ቲውተር በቻይና የተከፈቱ እና በሆንግ ኮንግ ተቃውሞ ዘሪያ ያልተገባ ብሎም ያልተረጋገጠ መረጃን ሲያናፍሱ ነበረ ያላቸውን 936 ገጾች ዘግቷል።ቲውተር በሆንግ ኮንግ ተቃውሞ ዙሪያ ፀብ ጫሪ የሆኑ ከ200ሺ ያላነሱ ገጾች እንዳሉም ገልጿል።የፌስቡክ የሳይበር ደህንነት ፓሊሲ ናትናኤል ግሊቸር ተመሳሳዩ እርምጃ ስለመወሰዱ ተናግረዋል።በቀጠለው የሆንግ ኮንግ ተቃውሞ ዙሪያ ቻይና ምዕራባዊያኑ በጉዳዩ ጣልቃ ለመግባት እየሰሩ ይገኛሉ ትላለች ። ሆኖም ግን ለ11 ተከታታይ ሳምንታት የሆንግ ኮንግ ሰልፈኞች ቤጂንግን እያወገዙ ይገኛል።ቻይና ተቃውሞን ከአሸባሪነት ጎራ ፈርጃዋለች።