ሚድሮክ ኢትዮጵያ በአዲስ አበባ ከተማ ለሚገኙ የመንግስት ት/ቤት ተማሪዎች ከ11 ሚሊየን ብር በላይ የሚገመት የደብተር ድጋፍ አድርጓል፡፡
በተጨማሪም ሚድሮክ ኢትዮጵያ የፊታችን ጳጉሜ 3 ለሚካሄደው ብሄራዊ የኩራት ቀን “አዲስ አበባ ቤቴ ፤ ኢትዮጵያዊነቴ ኩራቴ!” የሚል ፅሁፍ ያረፈበት 100 ሺ ትሸርቶችን አዘጋጅቶ ለከተማ አስተዳደሩ ለማስረከብ ቃል ገብቷል፡፡
የከተማ አስተዳደሩ ም/ከንቲባ ኢ/ር ታከለ ኡማ የሚድሮክ ኢትዮጵያ ለተማሪዎች ላደረገው የደብተር ድጋፍ በተማሪዎች ፣ በወላጆች እና በከተማ አስተዳደሩ ስም ምስጋናቸውን አቅርበዋል