መደበኛ ያልሆነ

ባለፉት 2 ቀናት ብቻ ተሽከርካሪዎችና ከ2. 3 ሚሊዮን ብር በላይ የኮንትሮባንድ እቃዎች ተያዙ።

የገቢዎች ሚኒስቴር እና የጉምሩክ ኮሚሽን ሕግን ለማስከበር እየሠሩት ባለው ሥራ ባለፉት ሁለት ቀናት ብቻ በተለያዩ የጉምሩክ የፍተሻ ኬላዎች የተለያዩ ኮንትሮባንድ ዕቃዎች መያዛቸው ተገልጿል።በዚህም መሠረት ነሐሴ 21 ቀን 2011 ዓ.ም የሰሌዳ ቁጥሩ ኦሮ 3-66095 የሆነ ሚኒባስ ግምታዊ ዋጋቸው 290 ሺህ ብር የሆኑ የተለያዩ አልባሳት ጭኖ ከአወዳይ ከተማ ወደ ምሥራቅ ሐረርጌ ሲንቀሳቀስ መያዙ ታውቋል።

በተመሳሳይ ቀን የሰሌዳ ቁጥሩ ድሬ 3-04756 የሆነ ሀይሉክስ መኪና ግምታዊ ዋጋቸው 80 ሺህ ብር የሆኑ የተለያዩ የኮንትሮባንድ ዕቃዎች ጭኖ ሲንቀሳቀስ በክልሉ ፖሊስ ኮንትሮባንድ መከላከል ቡድን ተይዟል።በዚያው ዕለት የሰሌዳ ቁጥር ሱማ 3-00607 የሆነ ተሽከርካሪ 1.5 ሚሊዮን ብር የሚገመት ኮንትሮባንድ ዕቃ ጭኖ ሲንቀሳቀስ አውበሬ መቆጣጠርያ ጣቢያ ላይ በቁጥጥር ስር መዋሉ ተገልጿል።ነሐሴ 22 ቀን 2011 ዓ.ም ደግሞ ሱማ 3-04446 የሚል ሐሰተኛ ታርጋ የለጠፈ ተሽከርካሪ ጂግጂጋ አካባቢ ሲንቀሳቀስ የኮንትሮባንድ መከላከል ሠራተኞች ከክልሉ ፖሊስ ጋር በመተባበር በቁጥጥር ስር ማዋላቸውን የገቢዎች ሚኒስቴር አስታውቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *