መደበኛ ያልሆነ

ኢትዮ ቴሌኮም ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን በአዲስ አበባ አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎትን በአዲስ አበባ አስጀመረ

ኢትዮ ቴሌኮም ያስጀመረው አዲሱ ፈጣን የኢንተርኔት ኤልቲኢ የተበለ መሆኑን በዛሬው እለት በሰጠው መግለጫ ያለመክታል፡፡

ይህ ኤልቲኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ቀደም ሲል ከነበሩት የ3ጂ የኢንተርኔት አገልግሎት በጣም ፈጣን እንደሆነ የኢትዮ ቴሌኮም ዋና ስራ አስፈፃሚ ወ/ሪት ፍሬህይወት ታምሩ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ይህ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ዛሬ በመዲናዋ መጀመሩን ይፋ ተደርጓል።

ወ/ሪት ፍሬህይወት እንደገለጹት ይህን የኤልቲኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት በአዲስ አበባ ደረጃ ለመጀመር ዋነኛ መነሻ የሆናቸው የደንበኞች ፍላጎት መሆኑን ገልጸዋል።

በአዲስ አበባ የኢንተርኔት አጠቃቀም በከፍተኛ ሁኔታ እያደገ መምጣቱን ኃላፊዋ ተናግረዋል፤ ባለፉት 6 ወራት ብቻ የኢንተርኔት ትራፊክ በ82 በመቶ አድጓል ብለዋል።

ይህ ኤልቲኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት 173 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደተደረገበት እና ከሁዋዌ ጋር በአጋርነት እንደተሰራ በመግለጫው ተጠቅሷል።

በቅርቡ የክልል ከተሞችም የእዚህ የኤልቲኢ ፈጣን የኢንተርኔት አገልግሎት ተጠቃሚ ይሆናሉ ሲሉ ኃላፊዋ ገልጸዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *