መደበኛ ያልሆነ

የጃፓን ተመራማሪዎች ለኤች.አይ.ቪ ኤድስ የሚሰጡ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒቶች ፤ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን እንዲረዳ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛል፡፡

የጃፓን ተመራማሪዎች ለኤች.አይ.ቪ ኤድስ የሚሰጡ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒቶች ፤ ለኮሮና ቫይረስ ህሙማን እንዲረዳ ለማድረግ እየሰሩ ይገኛል፡፡

የጃፓን መንግስት በላብራቶሪ ሙከራ ደረጃ መድሀኒትን መስጠት በሚቻልበት ሁኔታ ፍቃድ ሰጥቷል፡፡

የኮሮና ቫይረስን የኤች.አይ.ቪ የእድሜ ማራዘሚያ መድሀኒት የመከላከል ሀይል እንዳለው በተመራማሪዎች ታምኖበታል፡፡

በጃፓን በትላንትናው እለት ብቻ በኮሮና ቫይረስ 88 ሰዎች ተጠቅተዋል፡፡

በቻይና በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ባለፉት 24ሰዓታት ውስጥ የ132 ሰዎች ህይወት ያለፈ ሲሆን ፤ 1886 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

ከ74 ሺህ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ፤ አጠቃላይ የሟቾች ቁጥር 2000 ደርሷል፡፡

በኮሮና ቫይረስ ተይዘው ከሆስፒታሉ አገግመው መውጣት የቻሉ ሰዎች ቁጥር ደግሞ ከ 12ሺህ በላይ ተመዝግቧል፡፡

##################################################################################

የናይጄሪያ ወታደሮች ንብረትነቱ የባህር ላይ ጠላፊዎች መኖሪያ ቤት ናቸው የተባለ በርካታ ቤቶችን በእሳት አውድመዋል፡፡

በኒጀር ዴልታ 6 የባህር ላይ አጋቾች ከደህንነት ሀይሎች ጋር መታኮሳቸውን ተከትሎ ፤ የናይጄሪያ ወታደሮች ከ 20 በላይ መኖሪያ ቤቶችን ማውደማቸው ተሰምቷል፡፡

መኖሪያ ቤቶቹ በባህር ዳርቻው አቅራቢያ የሚገኙ ሲሆን ፤ የባህር ላይ ጠላፊዎቹ እንደሆነ ይታመናል፡፡

የምዕራብ አፍሪካ ባህር በነዳጅ ሀብት የበለፀገ ቢሆንም ፤ በባህር ላይ ጠላፊዎች የተነሳ የስጋት ቀጠና ውስጥ ከገቡ አካባቢዎች አንዱ ነው፡፡

አካባቢውን ከጠላፊዎች ስጋት ነፃ ለማድረግ የናይጄሪያ መንግስትን ከፍተኛ ዋጋ እያስከፈለ ይገኛል፡፡

#Bisratnews #Nigeria

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *