መደበኛ ያልሆነ

የካቲት 19፣2012

ሳዑዲ አረቢያ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የኡምራና የመዲና ጉዞን በጊዜያዊነት አገደች።በሀገር ቻይና ከ80ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ የተያዙ ሲሆን ከ2700 በላይ ሰዎች ለህልፈተ ህይወት ተዳርገዋል።

########
የኮሮና ቫይረስ አለብኝ ብሎ ላመለከተ ቻይና ልትሸልም ነው።

በቻይና ሁቢ ግዛት በምትገኝ ከተማ የኮሮና ቫይረስ ምልክት ይታይብኛል ብሎ ላመለከተና ቀጥሎም ቫይረሱ ለተገኘበት ሰው ቻይና 1400የአሜሪካን ዶላር(45ሺ ብር) እንደምትሸልም አስታውቃለች።የቫይረሱን መዛመት ለመግታት ያለመ እርምጃ ነው።

########

በኮሮና ቫይረስ ስጋት አሜሪካና ደቡብ ኮርያ ሊያደርጉት የነበረው የጦር ልምምድ ተሰረዘ።

########

ፊሊፒንሱ ፕሬዝዳንት ሮድሪጌ ዱተርቴ ያለ አሜሪካ ድጋፍ ሽብርተኝነትን መዋጋት እንችላለን ሲሉ ተናገሩ።

ዱተርቴ የአሜሪካን በፊሊፒንስ ጣልቃ ገብነት ከዘመነ ባራክ ኦባማ ጀምሮ እየተቹ ይገኛል።

በዚህም የተነሳ ፊሊፒንስ ፊቷን ከዋሽንግተን ወደ ቤጂንግ አዙራለች።

########

የአፍሪካ ህብረት የሰላምና ደህንነት ኮሚሽን 3000 ወታደሮችን በሳህል ቀጠና ሊያሰማራ መሆኑ ተሰማ።

ወታደሮቹ ከየት ሀገራት የተውጣጡ እንደሆነ አልተጠቀሰም። በጂሃዲስቶች ጥቃት የተነሳ ኒጀር፣ቡርኪናፋሶና ማሊ ከፍተኛ ዋጋ እየከፈሉ ይገኛል።

ፈረንሳይ ከ5000 በላይ ወታደሮቿን ማሰማራቷ ይታወሳል።

########

በናይጄሪያ ቦርኖ ግዛት አንድ የሀገሪቱ ወታደር 4 የስራ አጋሮቹን ከገደለ በኋላ ራሱን ማጥፋቱ ተሰምቷል።

በጉዳዩ ዙሪያ የናይጄሪያ መንግስት የማጣራት ስራን እያከናወነ ሲሆን ህይወታቸውን ያጡት ወታደሮች ቦኮሀራምን ለመዋጋት ግዳጅ የተሰጣቸው እንደነበር ተሰምቷል።

########

ከናይጄሪያ ተሰርቆ ወደ ሜክሲኮ ተወስዶ የነበረ ቅርስ ተመለሰ።

በ6ኛው ክፍለ ዘመን ከነሀስ የተሰራው ቅርስ ከናይጄሪያ ተሰርቆ ወደ ሜክሲኮ ቢወሰድም በሜክሲኮ የጉምሩክ ሰራተኞች በመያዙ ለባለቤት ሀገር ናይጄሪያ ተመላሽ ሆኗል።ይህ ውድ ቅርስ እንዴት ሊሰረቅ ቻለ በሚለው ዙሪያ ምርመራ ተጀምሯል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *