መደበኛ ያልሆነ

በሜክሲኳዊዉ የአደንዛዥ እጽ ዝዉዉር እና የወንጀለኛ ቡድን መሪ ኤል ቻፖ ስም አዲስ የቢራ ብራንድ መሰየሙን የኤል ቻፖ ሴት ልጅ አስታወቀች፡፡

የቢራዉ ስያሜ “El Chapo 701” የተባለ ሲሆን 701 ቁጥር የተመረጠዉ እ.ኤ.አ በ2009 ኢል ቻፖ የአለማችንን 701ኛ ቱጃሩ ሰዉ ነዉ ሲል የሀብታሞችን ዝርዝር የሚያወጣዉ ፎርብስ ማሳወቁን ተከትሎ ነዉ፡፡

ኤል ቻፖ 701 ቢራ 4% የአልኮል ይዘት ያለዉ ሲሆን በ355 ሚ ሊትር ጠርሙስ ቀርቧል፡፡

አንዱ ቢራ በ70 ፔሶ ወይም 120 ብር ቀርቧል፡፡
በሰሜንና ደቡብ አሜሪካ በግለሰቦች ስም ቢራ ማቅረብ የተለመደ ሲሆን በአርጀንቲና
የሚገኙ የፖለቲካ ፓርቲ መሪዎች በፓርቲያቸዉ ስም የቢራ ብራንድ አላቸዉ፡፡

አንዱ የፓርቲ አባል የሌላኛዉን ፓርቲ የቢራ ብራንድ አይጠጣም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *