መደበኛ ያልሆነ

በጣሊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ የ 133 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

በጣሊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ የ 133 ሰዎች ህይወት ማለፉ ተሰማ

የኮሮና ቫይረስ በክፍተኛ ፍጥነት በጣሊያን እየተዛመተ ሲሆን ባለፉት 24 ሰዓታት ብቻ 133 ሰዎች ሕይወታቸው ያለፈ ሲሆን የሟቾች ቁጥር 366 ደርሷል፡፡

በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በጣሊያን ብቻ 7375 ደርሷል፡፡ ይህንኑ ከትሎ የ 16 ሚሊየን ሰዎች መኖሪያ በሆነችው ሎምባርዲያ እና ሎሎች 14 ግዛቶች ልዩ ፍቃድ እስካልተሰጠ ድረስ መንቀሳቀስ ተከልክሏል፡፡

ጠ/ሚ ጁሴፔ ኮንቴ ት/ቤቶች ፣ ሙዚየም ፣ የስፖርት ማዘውተሪያ ማዕከላት (ጂም) ፣ የምሽት ቤቶች እና የመሰብሰቢያ አዳራሾች እስከ ሚያዝያ 3 ዝግ ሆነው እንደሚቀጥል ተናግረዋል፡፡ ከቻይና በመቀጠል ከፍተኛ ሰብዓዊ እልቂት ኮሮና በጣሊያን አድርሷል፡፡

ቫይረሱ በእድሜ የገፉ ሰዎች ላይ ከፍተኛ ጉዳት እያደረሰ ሲሆን እድሜያቸው ከ 65 ዓመት በላይ የሖኑ ሰዎች በብዛት የሚኖሩባ ጣሊያንን እየፈተናት ይገኛል፡፡

በመላው ዓለም በኮሮና የጠያዙ ሰዎች ቁጥር 107 ሺህ ሲደርስ 3600 ሰዎች ለህልፈተ ሕይወት ተዳርገዋል፡፡ በኢራን 6566 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ 194 ሰዎች ሕይወታቸው አልፏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *