መጋቢት 1፣2012
የብስራት ማለዳ መረጃዎች
በምሽት ጨዋታ አስቶን ቪላን በሜዳው ያስተናገደው ሌስተር ሲቲ 4 ለ 0 በማሸነፍ በደረጃ ሰንጠረዥ በ53 ነጥብ 3ኛ ደረጃ ላይ ተቀምጧል።
######
በጣሊያን በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 463 ደረሰ።
በሀገሪቱ በሚገኙ 20 ግዛቶች ቫይረሱ መስፋፋቱ ተነግሯል።ከመንግስት ልዩ ፍቃድ እስካልተሰጠ ድረስ ዜጎች ከመንቀሳቀስ እንዲቆጠቡ ትዕዛዝ ተላልፏል።
######
በዙምባብዌ በኮሮና ቫይረስ የተጠረጠረ የታይላንድ ግለሰብ ከሆስፒታል በድንገት ማምለጡ ድንጋጤን ፈጠረ።
ዚምባብዌ በቫይረሱ ስጋት ውስጥ ገብታለች።
######
በሩዋንዳ መዲና ኪጋሊ ተዘጋጅቶ የነበረ የሙዚቃ ኮንሰርት በኮሮና ስጋት የተነሳ ተሰረዘ።
በደቡብ አፍሪካ ከጣሊያን ለ10 በመሆን በቡድን ከመጡ ሰዎች መካከል በአራቱ ላይ ቫይረሱ ተገኝቷል።