መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 2፣2012

የራሺያው ፕሬዝዳንት ቭላድሚር ፑቲን እስከ 2036 ለቀጣዮቹ 16 ዓመታት ፤ በስልጣን ላይ መቆየት እንዲችሉ ህገ መንግስቱን የሚሻሻልበትን መንገድ እየተዘጋጀ መሆኑ ተሰማ

ከአራት ዓመታት በኋላ ቭላድሚር ፑቲን ከስልጣን እንደሚወርዱ ቢጠበቅም ፤ ነገር ግን በስልጣን ላይ እስከ 2036 ለመቀጠል እንዲችሉ ህገ መንግስቱን ለማሻሻል ለቂቅ ሀሳቡን ደግፈዋል፡፡

ፑቲን ስልጣናቸውን ህገ መንግስቱን በማሻሻል ለማስቀጠል መፈለጋቸው በተቺዎቻቸው ዘንድ ቅሬታ አስነስቷል፡፡

በወርሃ ሚያዝያ ፑቲን ስልጣናቸውን ለማራዘም የያዙትን ውጥን የሚደግፍ አልያም የሚቃረን ሀገር አቀፍ ምርጫ ይደረጋል፡፡

ፑቲን እ.ኤ.አ በ 2036 እድሜያቸው 83 ይደርሳል፡፡

ዋንኛው የፑቲን መንግስት ተቃዋሚ አሌክሲ ናቫኒባይ ፤ ፑቲን የእድሜ ዘመን ፕሬዝዳንት ለመባል እየተንደረደሩ ነው ብሏል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *