መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 11፣2012

የናጄሪያው ፕሬዝደንት ሙሀሙዱ ቡሃሪ ሴት ልጅ ከእንግሊዝ ትናንትና ምሽት መመለሷን ተከትሎ ራሷን አግላ እንድትቆይ መደረጉ ተሰማ፡፡

የፕሬዝዳንት ሙሃሙድ ቡሃሪ እና የቀዳማዊት እመቤት አይሻ ቡኃሪ ሴት ልጅ ፤ የቫይረሱ ምልክት ባይታይባትም ከቀናት በኋላ የተለየ ምልክት ሊኖር ስለሚችል ራሷን እንድታገል ተደርጓል፡፡

በእንግሊዝ የነበራትን ቢሮ በመዝጋት ወደ ሀገሯ ናይጄሪያ መመለሷም ተሰምቷል፡፡

ናይጄሪያ ባሳለፍነው እሮብ እንግሊዝና አሜሪካን ጨምሮ ወደ ሌሎች 11 ሀገራት የጉዞ ክልከላ ማድረጓ ይታወሳል፡፡

በአጠቃላይ በሀገሪቱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 12 ደርሷል፡፡

#########
#########

አጫጭር መረጃዎች

~ ፊሊፒንስ ከቀጣዩ እሁድ ምሽት አንስቶ የውጪ ሀገራት ዜጎች ወደ ሀገሬ አትምጡብኝ አለች።በሀገሪቱ 217 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

~ ስሪላንካ በቀጣይ ወር ልታካሂደው የነበረውን የህዝብ እንደራሴዎች ምርጫ ልታራዝመው እንደሆነ ተሰምቷል።

~ህንድ የህዝብ ትራንስፖርት ከልክላለች ጠቅላይ ሚንስትር ናሬንድራ ሞዲ ዜጎች በቤታቸው እንዲቆዩ መክረዋል።

~ሳዑዲ አረቢያ የሀገር ውስጥ በረራና የህዝብ ትራንስፖርት ከነገ ጠዋት ጀምሮ እንዳይንቀሳቀሱ ከልክላለች።በቫይረሱ ከ270 በላይ ሰዎች ተይዘዋል።

~በሜክሲኮ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 164 ደርሷል በ24 ሰዓታት ውስጥ በ46 ጨምሯል።

~በቬትናም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 85 መድረሱን ተከትሎ የውጪ ሀገራት ዜጎች ላይ የተጣለው የጉዞ ክልከላ ተጠናክሮ ቀጥሏል።

#########
#########

አርጀንቲና ከደቡብ አሜሪካ ሀገራት ቀዳሚ በመሆን ድንበሯን መዝጋቷን አስታወቀች።

የተያዘው የመጋቢት ወር እስኪጠናቀቅ ድረስ ፤ ምግብና መድሀኒት ለመግዛት እስካልሆነ ድረስ ከቤት መውጣት እንደማይቻል የአርጀንቲና መንግስት አስጠንቅቋል።

#########
#########

በጣሊያን የኮሮና ቫይረስ ያደረሰውን ከፍተኛ ሰብዓዊ እልቅቲ ተከትሎ ፖፕ ፍራንሲስ በቀጥታ ስርጭት የፀሎት ስነስርዓት እያከናወኑ ይገኛል።

#########
#########

ስፔን በመላው ሀገሪቱ የሚገኙ ሆቴሎች እንዲዘጉ ውሳኔ አሳልፋለች፡፡

በመላው ስፔን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 831 መድረሱን ተከትሎ ስፔን ከፍተኛ ስጋት ውስጥ ገብታለች፡፡

በአውሮፓ ከሚገኙ ሀገራት ከጣሊያን በመቀጠል ስፔን በቫይረሱ ክፉኛ ተጎጂ ሆናለች፡፡

በአውሮፓ ከፈረንሳይ በመቀጠል የቱሪስቶችን ቀልብ በመሳብ በሁለተኛ ደረጃ የምትቀመጠው ስፔን ቱሪስቶች ወደ ሀገሯ እንዳይመጡ ድንበሮቿን ዘግታለች፡፡

መንቀሳቀስን ዜጎች የተከለከሉ ሲሆን ፤ ከመኖሪያ ቤታቸው ሲመጡ የተገኙ 49 ሰዎች በቁጥጥር ስር ውለዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *