መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 11፣2012

እንግሊዛዊዉ ሰዉ ድብቅ ፍቅርን ለማሳለፍ ለባለቤቴ ሳይነግራት ወደ ጣሊያን ቢያመራም በኮሮና ቫይረስ መያዙ አጋልጦታል፡፡

በ30ዎቹ የመጨረሻ እድሜ ላይ እንደሆነ የተነገረዉ እንግሊዛዊዉ ሰዉ በጣሊያን ከሌላ ሴት ጋር የድብቅ የፍቅር ጊዜን ያሳልፋል፡፡በዚህ ጊዜ ታዲያ ለባለቤቱ ወደ ጣሊያን እንዳመራ አልነገራትም ነበር፡፡ በዛዉ በእንግሊዝ ከሚኖሩበት ከተማ ዉጪ ለስራ እንደሄደ
ነግሯት የነበረ ቢሆንም እርሱ ግን በጣሊያን ድብቅ የፍቅር ጊዜን ሲያሳልፍ ቆይቷል፡፡

በጣሊያን በነበረዉ ቆይታ በቫይረሱ ተይዟል፡፡ከጤናዉ ሁኔታ ይልቅ ለባለቤቱ መዋሸቱ ጭንቀት እንደፈጠረበት ተናግሯል፡፡

#########
#########

በ- #ኮሮና_ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ብዛት 9 መድረሱን የጤና ሚንስትር አስታወቀ።

#########
#########

ፍቅሩን ለመግለጽ የእጮኛዉን ምስል ለ24 ሰዓታት የተነቀሰዉ ሰዉ አነጋጋሪ ሆኗል፡፡

የ22 ዓመቱ ቬትናማዊ ወጣት ቫን ላም አብዝቶ ለሚወዳት የ29 ዓመቷ ፍቅረኛዉ ትራን ጀርባዉን በእርሷ ምስል እንዲህ ተነቅሷል፡፡ በሶስት ምዕራፍ የተነቀሰ ሲሆን ለመጀመሪያ ጊዜ ስምንት ሰዓታት የታቱ መርፌ ጀርባ ላይ ተሰክቶ ቆይቷል፡፡

ከዛም ለስድስት ሰዓታት በመቀጠል ለዘጠኝ ሰዓት መርፌዉ በጀርባዉ ላይ እንደተሰካ ቆይቷል፡፡በደረቱ ላይ ደግሞ
ስሟን እና የልደቷን ቀን ተነቅሷል እርሷም በዚህ ደስተኛ ሆናለች፡፡

#########
#########

ከኮሮና ቫይረስ 88,441 ሰዎች ማገገማቸው ተሰማ።በመላው አለም በቫይረሱ የተየዙ ሰዎች ቁጥር እስከ ዛሬ መጋቢት 11 ማለዳ ድረስ 245,850 ሲደርስ የ10,047 ሰዎች ህይወት አልፏል።

ራስዎን እና አካባቢዎን ከኮሮና ቫይረስ ይጠብቁ!

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *