መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 16፤2012- ብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች አጫጭር መረጃዎች


~ በደቡብ አፍሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 709 ደረሰ።የሀገሪቱ የጤና ሚንስቴር ከነበረበት 544 በ24 ሰዓታት ውስጥ ጭማሪ ማሳየቱን የገለፀ ሲሆን ከአህጉሩ ከፍተኛ ተደርጎ ተመዝግቧል።
~ ዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ በኮሮና ስጋት ወደ መዲናዋ ኪንሳሻ መግባትና መውጣት ተከለከለ።
~ በህንድ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ9 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 519 ሰዎች መያዛቸው ተረጋግጧል።
~ በአሜሪካ የኮሮና ቫይረስ መመርመሪያ እጥረት ማጋጠሙን ተከትሎ ደቡብ ኮርያ ልትለግስ መሆኑ ተሰማ።
~ ለቀጣዮቹ 21 ቀናት 1.3 ቢሊዮን የህንድ ነዋሪዎች በቤታቸው እንዲቆዩ መመሪያ ተላለፈ።

####################
በኮሮና ቫይረስ የተነሳ በቀጣይ ከፍተኛ ተጎጂ ሀገር አሜሪካ ልትሆን እንደምትችል የዓለም የጤና ድርጅት አስታወቀ፡፡
በአሜሪካ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በከፍተኛ ደረጃ የጨመረ ሲሆን 54‚867 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡ ከነዚህ መካከል የ782 ሰዎች ህይወት አልፏል፡፡
የኒውዮርክ ግዛት ገዢ አብድሬው ኩዋ አሜሪካ ከዚህ በላይ ተጎጂ ልትሆን እንደምትችል አስጠንቅቀዋል፡፡
በኒውዮርክ እና ካሊፎርኒያ ግዛቶች ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኮሮና ተጠቂዎች ተገኝተዋል፡፡

####################
በጋና በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር በእጥፍ ጨመረ
የጋና የጤና ባለስልጣን እንዳስታወቀው በአንድ ቀን 25 ግለሰቦች በቫይረሱ መያዛቸውን ተከትሎ በአጠቃላይ በበሽታው የተያዙ ሰዎች ቁጥር 52 ደርሷል፡፡
ህሙማኑ በለይቶ ማቆያ ስፍራ ህክምናቸውን እየተከታተሉ ይገኛል፡፡
ከግለሰቦቹ ጋር ንክኪ የነበራቸው 600 ሰዎች ተለይተው ምርመራ እየተደረገላቸው ነው፡፡
በጋና በትናንትናው እለት የ 2 ሰዎች ህልፈት መሰማቱ ይታወሳል፡፡

####################

በቬንዚዌላ ወላጆቻቸው በመሰደዳቸው የተነሳ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ህፃናት ወላጅ አልባ ሁነዋል፡፡
በኢኮኖሚ እየዳከረች ሰባት ዓመታትን ያስቆጠረችው ሀገሪቱ ከዚህ አስከፊ ችግር ለመላቀቅ ዜጎቿ ብቸኛ አማራጫቸው ስራ ፍለጋ ስደት አድርገዋል፡፡
በዚህ የተነሳ በመቶ ሺዎች የሚደርሱ ህፃናት ወላጅ አልባ የሆኑ ሲሆን ወዳጅ፣ዘመድ እንዲሁም መሰል ጎደኞቻቸው ጋር ለመጠጋት ተገደዋል፡፡
መጠጊያ ያጡ ህፃናት ደግሞ በህገወጥ የህፃናት አዘዋዋሪዎች እስከመውደቅና ለወሲብ ንግድ እስከመሰማራት እየደረሱ ይገኛል ስትል የኒውዮርኳ ዘጋቢ ጁሊ ቱርክዊትዝ ፅፋለች፡፡
ከስር የምትመለከቱት ምስል በቬንዙዌላ ማራካይቦ የስምንት ዓመቱ ጂን ካርሎስ እናቱ ፈርናንዴስን ወደ አውቶቡስ መሳፈሪያ እየሸኝ በመጨረሻዎቹ የስንብት ደቂቃዎች ላይ በሜርዲት ኮሁት የተነሳ ነበር፡፡
የአስር ዓመቷ እህቱ ክሪሶል እንዲሁም የ 12 ዓመቱ ክሪስቲያን ይህንን የመጨረሻ አሳዛኝ ክስተት ላለማየት ከቤታቸው ይገኛሉ፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *