🇮🇹በጣሊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የ683 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ በጣሊያን ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 7503 ደርሷል። በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 74,386 ደርሷል።
################################
በጣልያን በኮሮና ቫይረስ የተነሣ ቢያንስ 50 ቄሶች ህይወታቸው ማለፉ ተሰማ።
################################
በአፍጋኒስታን መዲና ካቡል በዛሬው እለት ለተፈፀመው የአጥፍቶ ጠፊ ጥቃት አይኤስ አይኤስ ሀላፊነቱን እንደሚወስድ አስታወቀ። በጥቃቱ 25 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።
################################
በፍልስጤም በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የመጀመሪያው ሞት ሪፖርት ተደርጓል። በዌስት ባንክ የ60 ዓመት እድሜ ያላት ግለሰብ ህይወቷ አልፏል።
በጋዛ ሰርጥ እንል በዌስት ባንክ 62 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ተረጋግጧል::
################################
በኮሮና ቫይረስ ከተያዙት ሰዎች 113,120 ሰዎች ማገገማቸው ተሰማ።
በመላው አለም በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 452,168 ሲደርስ 20,494 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል።