መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 17፤2012- ብስራት ማለዳ አጫጭር መረጃዎች

አጫጭር መረጃዎች

~ የዩጋንዳ ፕሬዝዳንት ዩዌሪ ሙሴቬኒ ለ14 ቀናት የህዝብ የትራንስፖርት አገልግሎት ላይ ልክከላ አደረጉ።የግል ተሽከርካሪዎች ከሶስት ሰው በላይ ማሳፈር እንደማይችሉ ገልፀዋል።

~ በቱኒዚያ በኮሮና ቫይረስ በ24 ሰዓት ውስጥ 59 ሰዎች መያዛቸው ሪፖርት ተደረገ።በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 173 ደርሷል።

~ በደቡብ ኮርያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 9,241 ደረሰ።ከነዚህ መካከል 131 ሰዎች ህይወታቸው አልፏል

~ የራሺያ መንግስት ከነገ ጀምሮ የመንገደኞች በረራን ሰረዘ።የራሺያ አየር መንገድ የሀገሪቱ ዜጎች ወደ ሀገራቸው መመለስ ለሚገልጉ ብቻ በረራ እንደሚያደርግ አስታውቋል።

~ እንግሊዝ ለህክምና ባለሙያዎች መኪናቸውን ያለ ፓርኪንግ ክፍያ በነፃ እንዲያቆሙ ፈቅዳለች።በሀገሪቱ በቫይረሱ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 465 ደርሷል።

~ በሜክሲኮ በዛሬው እለት እንቅስቃሴ እንዲገደብ ተደርጓል።በቫይረሱ 475 ሰዎች ሲያዙ የስድስት ሰዎች ህይወት አልፏል።

የብርቱካን ጭማቂ ዋጋ በከፍተኛ ሁኔታ አሻቅቧል

በአውሮፓና አሜሪካ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ የብርቱካን ጭማቂ ዋጋ በ 20 በመቶ ከፍ ስለማለቱ ተሰምቷል፡፡

ይሁንና የፈላጊዎች ቁጥር ከፍ ቢልም አቅርቦቱን ተደራሽ ለማድረግ የትራንስፖርት ገደቡ ለአቅራቢዎች ፈተና ሁኖባቸዋል፡፡ እንደ ሀገራችን ኢትዮጵያ ሁላ ሌሎቹም ሀገራት በሽታውን ለመከላከል ፍቱን ነው ያሉትን አማራጮች ሁላ በመጠቀም ላይ ይገኛሉ፡፡

ይሁንና ግን የህክምና ባለሙያዎች እስካሁን በዚህ ረገድ በጥናት የተደገፈ መረጃን ይፋ አላደረጉም፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *