መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 17፤2012- ብስራት አመሻሽ አጫጭር መረጃዎች

ጣሊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የ662 ሰዎች ህይወት አለፈ!

በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ በጣሊያን ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 8,165 ደርሷል።በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 80,539 ደርሷል።

##############
##############

በኬንያ የመጀመሪያው የኮቪድ-19 ሞት ተመዘገበ!

የኬንያ ጤና ሚኒስቴር እንዳስታወቀው ዛሬ ከሰዓት በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] የተጠቃ አንድ 66 ዓመት ኬንያዊ ዜጋ ህይወቱ አልፏል።

ምንጭ፦ የኬንያ ጤና ሚኒስቴር

##############
##############

ቻይና ለውጪ አገር ዜጎች ድንበሯን ዝግ አደረገች!

የቻይና መንግሥት የኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] ስርጭትን ለመግታት የውጪ አገር ዜጎች ወደ አገሪቱ እንዳይገቡ ክልከላ አድርጓል።

የቻይና መንግሥት ከዚህ ውሳኔ የደረሰው በአሁኑ ወቅት በኮሮና ቫይረስ [ኮቪድ-19] መያዛቸው የሚረጋገጡ ሰዎች ፤ ከሌሎች አገራት ወደ ቻይና የገቡ እንጂ በቻይና የሚገኙ ሰዎች ባለመሆናቸው ነው ተብሏል።

ምንጭ፦ ቢቢሲ

##############
##############

ፊሊፒንስ ውስጥ 9 ዶክተሮች በኮሮና ቫይረስ ተጠቅተው መሞታቸው ተሰምቷል። የሰዎችን ህይወት ለማትረፍ ከፍተኛ ትግል እያደረጉ ያሉት የፊሊፒንስ የጤና ባለሞያዎች በቂ መከላከያ እያገኙ አይደለም ተብሏል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *