አጫጭር መረጃዎች
~ የቡድን 20 አባል ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ክፉኛ የተጎዳው የአለም ኢኮኖሚ እንዲያገግም የ5 ትሪሊዮን የአሜሪካን ዶላር ድጋፍ ለማድረግ ቃል ገቡ።
~ ጀርመን በኬንያ ለጠፋው ስድስት ሚሊየን የፊት የአፍና አፍንጫ መሸፈኛ ጭምብል እጄ ላይ ስላልደረሰ አልከፍልም ብላለች።
~ በካሜሮን የሚገኙ አማፂያን የኮሮና ቫይረስን ለመዋጋት የተኩስ አቁም ስምምነት ላይ ደረሱ።
~ በአፍጋኒስታን የኮሮና ቫይረስ የ100ሺ ሰዎችን ህይወት ሊነጥቅ እንደሚችል መንግስት አሳሰበ።ከ34 የሀገሪቱ ግዛቶች በ29ኙ ቫይረሱ ተሰራጭቷል።
~ የፍልስጤም አስተዳደር የቫይረሱ ስርጭትን ለመግታት ድጋፍ እንዲደረግለት ጥሪ አቀረበ።86 ሰዎች በቫይረሱ ሲያዙ የ1 ሰው ህይወት አልፏል።
~ ዶናልድ ትራምፕ በወርሃ ነሀሴ የሚካሄደውን የሪፓብሊካን ብሄራዊ ጉባሄ እንደማይሰርዙ አስታወቁ።ጉባሄው በሰሜናዊ ካሮላይና ይካሄዳል።
~ የጃፓን ጠቅላይ ሚንስትር ሺንዞ አቤ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አያስፈልገንም ኢኮኖሚውን ክፉኛ ይጎዳል ሲሉ ተናገሩ።
~ በፓኪስታን በሶስት ሳምንት ውስጥ ብቻ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 1,057 ደርሷል።