መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 19፤2012- ብስራት የምሽት አጫጭር ወሬዎች

የአሜሪካ የምግብና የመድኃኒት አስተዳደር ለፈጣኑ የኮሮና መመርመሪያ መሳሪያ እውቅና ሰጠ።
በአብቦት ላብራቶሪ የተሰራው መሰሪያ የኮሮና ፖዘቲቭ ውጤትን በ5 ደቂቃ ኔጌቲቭ ውጤትን ደግሞ በ13 ደቂቃ ያሳውቃል።በቀጣዩ ሳምንት በየእለቱ የመመርመሪያ መሳሪያው 50ሺ ያህል ሽያጭ ይጠበቃል።
##################################
በጣሊያን በ24 ሰዓታት ውስጥ ብቻ የ889 ሰዎች ህይወት አለፈ!
በአጠቃላይ በኮሮና ቫይረስ በጣሊያን ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 10,023 ደርሷል።በቫይረሱ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 92,472 ደርሷል።
##################################
በኮሮና መጠቃቱን ሚስጥር ያደረገው ዶክተር ህይወቱ ማለፉ ተሰማ
በማዕከላዊ እስያ የኡዝቤኪስታን ዜጋ የሆነው የ39 ዓመቱ ዶክተር በኮሮና ቫይረስ መያዙን ሚስጥር በማድረግ ራሱን ለማከም ያደረገው ጥረት ሳይሳካ በዛሬው እለት ህይወቱ አልፏል።ከረፈደ ወደ ጤና ተቋም ቢያመራም ማትረፍ ግን አልተቻለም።

##################################
አጫጭር መረጃዎች
~ የኒውዮርክ ከተማ ሆስፒታሎች ለህክምና አገልግሎት የሚውሉ መሳሪያዎች እጥረት እንዳጋጠማቸው ተሰምቷል።በከተማዋ ብቻ 510 ሞት ሲመዘገብ ከ45ሺ በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።
~ በእንግሊዝ በኮሮና ቫይረስ የተነሣ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 1,019 ደርሷል።በስኮትላንድ 40፣ በዌልስ የ38 ሰዎች ህይወት አልፏል።
~ የኢራኑ ፕሬዝዳንት ሀሰን ሩሃኒ የሀገሪቱ የጤና መሰረተ ልማት የመጣውን ችግር የመቀልበስ አቅም አለው ሲሉ ተናገሩ።በኢራን በኮሮና እስካሁን ድረስ ባሉ መረጃዎች የ2,517 ሰዎች ህይወት አልፏል።
~ ህንድ የኮሮና ቫይረስን ለመመከት ቢያንስ 38 ሚሊየን የአፍና የአፍንጫ መሸፈኛ ማስክ እንደሚያስፈልጋት አሳወቀች።
~ በሲንጋፖር በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 802 ደረሰ።በዛሬው እለት ብቻ በሲንጋፖር 70 ሰዎች በቫይረሱ መያዛቸው ሪፖርት ተደርጓል።
~ በሩሲያ በኮሮና ቫይረስ የሚያዙ ሰዎች ቁጥር ጨመረ።በ24 ሰዓት ውስጥ 228 ሰዎች በቫይረሱ ሲጠቁ በአጠቃላይ የተጠቂዎች ቁጥር 1,264 ደርሷል።
~ በጃፓን የአካል ጉዳተኞች ማዕከል ቺባ 57 የኮሮና ቫይረስ ተጠቂዎች ተገኝተዋል።

##################################

“የምናደንቃት ታላቅ አርቲስታችን ሐመልማል አባተ ገዳ መኖሪያ ቤቷን እንድንጠቀምበት ሰጥታናለች።
በማስተማር፣ የሰውን ሰብዕና በመቅረፅ ትልቅ ቦታ የምንሰጣቸው ከያንያን ከዚያ አልፈው ደግሞ ካላቸው ጥሪት ማካፈላቸው እጅግ ተምሳሌነት ያለው ተግባር ነው።
ክበሪልን እህታችን ሐመልማል።እጅግ እናመሰግናለን።”

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *