መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 21፤2012- ብስራት የምሽት አጫጭር ወሬዎች

አጫጭር መረጃዎች

~ የ11 አውሮጳ ሀገራት መንግስታት በወሰዱት ፈጣን እርምጃ የ59ሺ ሰዎች ህይወት ከኮሮና መታደጋቸውን በለንደን የኢምፔሪያል ኮሌጅ ሙሁራን ገለፁ።

~ በስፔን በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 7,340 ደርሷል።የቫይረሱ ተጠቂዎች ቁጥር 85ሺ መድረሱን ተከትሎ ከቻይና በዛሬው እለት በልጧል።

~ በኬንያ በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 50 ደርሷል።በየእለቱ በሀገሪቱ ምርመራ እየተደረገላቸው ያሉ ሰዎች ቁጥር ከ300 እንደማይበልጥ የኬንያ ጤና ሚንስቴር አስታውቋል።

~ በግብፅ ድመት የኮሮና ቫይረስን ታስተላልፋለች መባሉን ተከትሎ በርካታ ግብፃዊያን ድመቶቻቸውን እየገደሉ ይገኛል።ድርጊቱን ተከትሎ በአለም የጤና ድርጅት ያልተረጋገጠ በመሆኑ ግብፃውያኑ ድመቶቻቸውን ከመግደል እንዲቆጠቡ ጥሪ ቀርቧል።

~ በእንግሊዝ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 1,284 መድረሱን የእንግሊዝ ብሄራዊ የጤና ኤጀንሲ አስታወቀ።

~ የእስራኤል ጠቅላይ ሚንስትር ቤንያሚን ኔታናሁ የኮሮና ምርመራ ውጤት ፖዘቲቭ ከሆነ አብረዋቸው የነበሩት የተቃዋሚ ፓርቲ የብሉና ዋይት መሪዎች በቫይረሱ ሊያዙ እንደሚችል ተሰግቷል።የኔታናሁ የቅርብ የስራ አጋር በቫይረሱ መያዙን ተከትሎ ኔታናሁ ራሳቸውን አግለዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *