አጫጭር መረጃዎች
~ በጃፓን መዲና ቶክዮ 78 ሰዎች በዛሬው እለት በኮሮና ቫይረስ መጠቃታቸው ሪፖርት ተደረገ።የቶክዮ ከተማ ገዢ ዩሪኮ ኮአይኪ ቫይረሱ ከተቀሰቀሰበት ጊዜ አንስቶ በከፍተኛ ፍጥነት የተዛመተው በዛሬው እለት ነው ሲሉ ተናግረዋል።
~ ፈረንሳይ፣ጀርመን እና እንግሊዝ ለኢራን የህክምና ቁሳቁስ መላካቸው ተሰማ።በኢራን በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የሟቾች ቁጥር 2,898 ደርሷል።
~ በአማዞን የመላላክ ስራ ውስጥ የተሰማሩ ዜጎች የቫይረሱ ተጠቂ ልንሆን እንችላለን ሲሉ ቅሬታ አቀረቡ።በቂ የመከላከያ ቁሳቁስ አልቀረበልንም ሲሉ የጣሊያን እና አሜሪካ የአማዞን ሰራተኞች ተናግረዋል።የዩናይትድ ስቴትስ በርካታ ሴናተሮችም ስጋታቸውን ለአማዞን ባለቤት ጄፍ ቤዞስ ገልፀዋል።
~ የኢምሬት አየር መንግደ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ ከደረሰበት ኪሳራ መውጣት እንዲችል ድጋፍ እንደሚደረግለት የዱባዩ አልጋ ወራሽ ልዑል ሼኪ ሀማዳን ቢን ሞሃመድ ተናገሩ።
~ በአምስትት የገልፍ ሀገራት በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 21 ሲደርስ 4ሺ ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።ሀገራቱም ሳዑዲ አረቢያ፣ኢምሬቶች፣ኩዌት፣ባህሬን እና ኦማን ናቸው።
~ የሞዛምቢክ መንግስት የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመቀነስ ከነገ መጋቢት 23 የሚጀምር የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አሳለፈ።
~ በቱርክ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት በሚል የፕሬዝዳንት ኤርዶሃን አስተዳደር 45ሺ ታራሚዎችን ሊፈታ መሆኑን አስታወቀ።