መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 23፤2012- ብስራት የምሽት አጫጭር መረጃዎች

አጫጭር መረጃዎች

~ የኮሮና ቫይረስን ለመከላከል በጀርመን እንቅስቃሴን የሚገድበዉ ህገ ለቀጣዮቹ 18 ቀናት እንደሚቀጥል መራሂተ መንግስት አንጌላ ሜርኬል አስታቀቁ፡፡በጀርመን በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ812 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 74‚508 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

~ ከሁለተኛዉ የአለም ጦርነት በኃላ ዊምብልደን የሜዳ ቴኒስ ዉድድር ለመጀመሪያ ጊዜ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ዉድድሩ ተሰረዘ፡፡

~ በኮሮና ቫይረስ ስጋት የተነሳ በሶማሊያ መዲና ሞቃዲሾ በሚገኘዉ ታዋቂዉ የሊዶ የባህር ዳርቻ ሰዎች እንዳይዋኙበት ተከለከለ፡፡

~ በሰርቢያ እዉቅ የቀኝ ክንፍ ፖለቲከኛ እና የአካባቢ ሚንስትር የሆኑት ባላዚክ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ህይወታቸዉ ማለፉ ተሰማ፡፡በሰርቢያ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ የ30 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 1‚060 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

~ የኩባ ኮሚንስት መንግስት ከአንድ ወር በኃላ የሚከበረዉ የላብ አደሮች ቀን በኮሮና ስጋት የተነሳ እንደማይከበር አስታወቀ፡፡በኩባ 6 ሰዎች በቫይረሱ ህይወታቸዉ ሲያልፍ 200 ሰዎች ደግሞ በቫይረሱ ተይዘዋል፡፡

~ የካናዳው ጠቅላይ ሚንስትር ጀስቲን ቱሩዶ ህግ አውጪውን አካል በመጥራት ከፍተኛ የተባለውን የጥቅል ድጋፍ እርዳታ እንዲያፀድቅላቸው ፍላጎት እንዳላቸው አስታወቁ።

~ በመላው አለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር 910ሺ ሲደርስ 45,498 ሰዎችን ህይወት ነጥቋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *