መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 25፤2012- ብስራት የምሽት አጫጭር መረጃዎች

አጫጭር መረጃዎች

~ የኬንያ ከፍተኛ የመንግስት ባለስልጣን ከጀርመን ወደ ሀገራቸው ሲመለሱ የኮሮና ቫይረስ ይገኝባቸውና ወደ ለይቶ ማቆያ ይገባሉ።ከቫይረሱ አሁን ላይ ቢያገግሙም በለይቶ ማቆያ ውስጥ ላለው ህግ ተገዢ ባለመሆናቸው የተነሣ ክስ እንደሚመሰረትባቸው ተሰማ።

~ በኖርዌይ በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ከሰራተኛው ህዝብ 14.7 በመቶ ያህሉ በከፊልና ሙሉ ለሙሉ ስራ አጥ መሆኑን የኖርዌይ መንግስት ይፋ አደረገ።

~ ታይላንድ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመከላከል ከነገ ቅዳሜ ጠዋት እስከ ሰኞ ከሰዓት ሁሉንም የመንገደኞች አውሮፕላን ከለከለች።በታይላንድ 19 ሞት ሲመዘገብ 1,978 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

~ በመላው አለም በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 58,392 ደረሰ።አምስቱ በርካታ ዜጎቻቸውን በቫይረሱ የተነጠቁ ሀገራት እንደ ቅደም ተከተላቸው ጣለያን፣ስፔን፣አሜሪካ፣ፈረንሳይና እንግሊዝ ናቸው።

~ የቱርክ ፕሬዝዳንት ኤርዶሃን እንዳስታወቁት ከዛሬ ምሽት ጀምሮ የኮሮና ቫይረስ ስርጭትን ለመግታት የ31 የቱርክ ከተሞች ድንበር ዝግ ተደርጓል።እድሜያቸው ከ20 ዓመት በታች የሆኑ ዜጎች ከቤት እንዳይወጡ ተከልክለዋል።በቱርክ በቫይረሱ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 425 ሲደርስ ከ20ሺ በላይ ሰዎች ላይ ቫይረስ ተዛምቷል።

~ በሩሲያ የኮሮና ቫይረስ ስርጭት መጨመሩን ተከትሎ ከዛሬ ሌሊት አንስቶ የሀገር ውስጥ እና የውጪ በረራ በጊዜያዊነት ታገደ።

~ የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የሰብዓዊ መብት ተሟጋቾች በኢራን ማረሚያ ቤቶች የኮሮና ቫይረስ እንዳይዛመት ያሰጋል ሲሉ ተናገሩ።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *