መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 28፤2012

ከ12ሺ በላይ ታራሚዎች ይቅርታ ተደረገላቸው

የደቡብ ክልል ጠቅላይ አቃቤ ህግ ዛሬ በሰጠው መግለጫ እንዳስታወቀው የክልሉ መስተዳድር ምክር ቤት ባስተላለፈው ውሳኔ መሰረት በመደበኛና በልዩ ሁኔታ ከተለያዩ የክልሉ ማረሚያ ቤቶች 12,553 ታራሚዎች ይቅርታ ተደርጎላቸዋል።

በመደበኛ መንገድ የይቅርታ ተጠቃሚዎችን መረጣና ምልመላ መስፈርት መሰረት ባደረገ መልኩ በአግባቡ የታረሙ ፣ መልካም ስነ ምግባር ያሳዩ 3,519 ወንድና 119 ሴት እንዲሁም 4 የእስራት ቅነሳ የተረገላቸው በድምሩ 3,642 ታራሚዎች ተጠቃሚ ሆነዋል።

የደቡብ ክልል መንግስት የኮሮና ቫይረስ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ መከሰትን ተከትሎ የቫይረሱን ስርጭት ለመቆጣጠርና ሊደርስ የሚችለውን አደጋ ለመቀነስ በልዩ ሁኔታ 8,601 ወንድና 310 ሴት በድምሩ 8,911 ታራሚዎች እንዲፈቱ ተደርጓል።

በተለይም ደግሞ ነፍሰ ጡሮች ፣ ህጻናት ያላቸው ፣ ልዩ ልዩ ህመም ያለባቸው፣ እድሜያቸው የገፋ፣ ከ18 አመት በታች የሆኑና አመክሯቸው የተቃረበ ግለሰቦች እንዲወጡ ተደርጓል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *