መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 28፤2012

የወርቅ ፣ቆዳ እና የቁም እንስሳት የውጪ ምንዛሬ ገቢ ከተያዘው እቅድ አንፃር ከ50 በመቶ በታች ዝቅተኛ ገቢ ተመዘገበ።

በ2012 በጀት ዓመት ባለፉት ስምንት ወራት ከወጪ ንግድ 1 ነጥብ8 ቢሊየን የአሜሪካ ዶላር ገቢ መገኘቱን የንግድና ኢንዱስትሪ ሚንስቴር የኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዳይሮክቶሬት ዳይሬክተር አቶ ወንድሙ ፍላቴ ለብስራት ሬድዮ ተናግረዋል።

ገቢው ካለፈው አመት ተመሳሳይ ጊዜ ጋር ሲነፃፀር የ10 በመቶ ብልጫ አለው።ሆኖም ግን የወርቅ ፣ቆዳ እና የቁም እንስሳት የውጪ ምንዛሬ ገቢ ከታቀደው በታች ሆኗል።

ትግስት ላቀው

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *