መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 30:2012 ዓ.ም

በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ የተለያዩ የቢሮ ዕቃዎችን ሰርቀው ሲያጓጉዙ የነበሩት 2 ግለሰቦች በቁጥጥር ስር አውሎ ምርመራ እያጣራባቸው መሆኑን የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን
ገለፀ፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በቁጥጥር ስር የዋሉት መጋቢት 23ቀን 2012 ዓ/ም በምሽቱ ክ/ጊዜ
በአዲስ ከተማ ክ/ከተማ ወረዳ 1 ልዩ ቦታው አሜሪካን ግቢ ተብሎ በሚጠራው አካባቢ
ነው፡፡

ሁለት ተጠርጣሪዎች ጨለማ ተገን በማድረግ የተለያዩ ማህተሞች ፣ፕሪንተሮች፣ ዴስክ
ቶፕ እና ለምን አገልግሎት እንደሚውል በውል ያልታወቀ 2 ማሽን ሰርቀው ለመሰወር
ሲሞክሩ በህብረተሰቡ ጥቆማ መያዙን የመርካቶ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ ወንጀል መከላከል
ኃላፊ ም/ኢ/ር እዮብ ተከተል ገልፀው ተሰረቅኩኝ ብሎ የሚያመለክት ግለሰብ በአካል
መቅረብ የሚችል መሆኑን አስታውቀል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *