መደበኛ ያልሆነ

መጋቢት 30:2012 ዓ.ም

አጫጭር መረጃዎች

~ በኬንያ በዛሬው እለት ቀጠሮ ተይዞለት የነበረው የህዝብ እንደራሴዎች ስብሰባ መሰረዙን አፈ ጉባዔው ጀስቲን ሙቱሪ ተናግረዋል።ስብሰባው ሊሰረዝ የቻለው ፕሬዝዳንት ኧሁሩ ኬንያታ የጉዞ ማዕቀብ በመላው ሀገሪቱ መጣላቸውን ተከትሎ ነው።

~ የኦማን ሱልጣን ሀቲሀም ቢን ታሪቅ አል ሰይድ ለ599 ታራሚዎች ኮሮናን በማስመልከት ይቅርታ መደረጉን አስታወቁ።ከነዚህ መካከል 366ቱ የውጪ ሀገራት ዜጎች ናቸው።

~ በሰሜን ኮርያ የኮሮና ምርመራ የተደረገላቸው 709 ሰዎች ከቫይረሱ ነፃ መሆናቸውን የአለም የጤና ድርጅት አስታወቀ።ሰሜን ኮርያ ቫይረሱ ከተስፋፋባቸው ደቡብ ኮርያና ቻይና ጋር ድንበር ብትጋራም አንድም በቫይረሱ የተያዘ ሰው የለም ብላለች።

~ የሆንግ ኮንግ አስተዳደር ለቀጣዮቹ 15 ቀናት ከ4 በላይ ሆኖ መሰብሰብን ጨምሮ የምሽት ቤቶችና መጠጥ ቤቶች ተዘግተው እንዲቆዩ የሚያስገድደውን ውሳኔ አራዘመ።

~ በፔሩ ሁለት ነፍሰ ጡር እናቶች በኮሮና ቫይረስ ቢጠቁም ከቫይረሱ ነፃ የሆኑ ህፃናትን መውለዳቸው ተሰምቷል።በፔሩ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 107 ሲደርስ ከ1300 በላይ ሰዎች በቫይረሱ ተጠቅተዋል።

~ በመላው አለም በኮሮና ቫይረስ የተነሳ ህይወታቸው ያለፉ ሰዎች ቁጥር 82,210 ደረሰ።ከፍተኛ የሞት መጠን የተመዘገበባቸው ሀገራት እንደ ቅደም ተከተላቸው ጣልያን፣ስፔን፣አሜሪካ፣ፈረንሳይ እና እንግሊዝ ናቸው።

~ በዲሞክራቲክ ሪፐብሊክ ኮንጎ የኮሮና ቫይረስ ስጋትን ተከትሎ 1,200 ታራሚዎች ከእስር ተለቀቁ።በሀገሪቱ የ18 ሰዎች ህይወት ሲያልፍ 180 ሰዎች በቫይረሱ ተይዘዋል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *