አጫጭር መረጃዎች
~ በህንድ የሚገኙ ግዙፍ ባቡሮች ወደ ለይቶ ማቆያ ማዕከልነት እየተቀየሩ ሲሆን 40ሺ አልጋ የመያዝ አቅም እንዳላቸው ተነግሯል።በህንድ በኮሮና ቫይረስ ህይወታቸውን ያጡ ሰዎች ቁጥር 178 ደርሷል።
~ በኒው ዮርክ የኮሮና ቫይረስ በስፋት የተሰራጨው ከአውሮጳ በመጡ መንገደኞች ስለመሆኑ ኒው ዮርክ ታይምስ ዘግቧል።
~ ከስድስት ቀናት በኋለ በኦስትሪያ እና ቼክ ሪፐብሊክ አነስተኛ ሱቆች እንደሚከፈቱ የተነገረ ሲሆን ዴንማርክ በበኩሏ ከስድስት ቀናት በኋላ ትምህርት ቤቶች እንደሚከፈቱ አስታውቃለች።የጀርመን የጤና ሚንስትር ሲፋሀን ከፋሲካ በዓል በኋላ ነገሮች ቀስ በቀስ ወደ ነበሩበት ይመለሳሉ ብለዋል።
~ በእስያ ግዙፉ ከተሞች የትራፊክ እንቅስቃሴ በከፍተኛ ደረጃ መቀነሱ ተሰማ።በፊሊፒንስ ማኒላ 96%፣በህንድ ዴህሊ 59%፣በኢንዶኔዥያ ጃካርታ 48%፣በታይላንድ በተመሳሳይ የትራፊክ እንቅስቃሴ 31 በመቶ ካለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ተቀዛቅዟል።
~ የኮሮና ቫይረስ 500 ሚሊየን የአለም ህዝብን ለረሃብ ሊዳርግ እንደሚችል የኦክስፋም ጥናት አምላክቷል።በቀጣዩ ሳምንት ወሳኝ የተባለ ውይይት በአለም ባንክ፣በአለም የገንዘብ ተቋም እና በቡድን 20 አባል ሀገራት የፋይናንስ ሚንስትሮች መካከል ይካሄዳል።
~ በመላው ዓለም በኮሮና ቫይረስ የተያዙ ሰዎች ቁጥር ከ1.5 ሚሊየን በላይ ሲሆን የ88,656 ሰዎች ህይወት አልፏል።332 ሺ ሰዎች ከቫይረሱ አገግመዋል።