መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 1፣ 2012 ዓ.ም

የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ነገ በአስቸኳይ ጊዜ አዋጁ ዙሪያ ለመምከር ለልዩ ስብሰባ ተጠሩ።

በኮሮና ቫይረስ ምክንያት መደበኛ ስራውን አቁሞ የነበረው ይህ ምክር ቤት ትናንት የሚኒሰትሮች ምክር ቤት ባሳለፈው የአስቸኳይ አዋጅ ዙሪያ ለመምከር ልዩ ስብሰባ እንደሚያደረግ አስታውቋል።የምክር ቤቱ ህዝብ ግንኙነት ክፍል እንዳስታወቀው 5ኛው የሕዝብ ተወካዮች ም/ቤት 5ኛ ዓመት የስራ ዘመን 2ኛ ልዩ ስብሰባ ነገ ሚያዝያ 02 ቀን 2012 ዓ.ም ይካሄዳል፡፡

ልዩ ስብሰባው የሚኒስትሮች ምክር ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝ ስርጭትን ለመከላከል፣ ለመቆጣጠር እና የሚያስከትለውን ጉዳት ለመቀነስ ያወጣውን የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ እና የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ አፈጻጸም መርማሪ ቦርድ አባላት ለመሰየም የቀረበውን የውሳኔ ሀሳብም መርምሮ ያፀድቃል ተብሎ ይጠበቃል፡፡

በተጨማሪም በኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ ሪፐብሊክ እና በአለም አቀፍ የልማት ማህበር መካከል ለኮሮና ቫይረስ አስቸኳይ ጊዜ ምላሽ ፕሮጄክት ማስፈጸሚያ የተደረገውን የብድር ስምምነት ለማጽደቅ የቀረበ ረቂቅ አዋጅን መርምሮ ያፀድቃል።

በትላንትናው እለት በሚንስትሮች ም/ቤት የኮሮና ቫይረስ ወረርሽኝን ለመግታት ኢትዮጵያ የአስቸኳይ ጊዜ አዋጅ ተግባራዊ ማድረግ እንደሚያስፈልጋት በተደረሰው ስምምነት መሠረት በጠቅላይ ሚኒስትር ዶ/ር አብይ አህመድ መግለጫ መሰጠቱ ይታወሳል።

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *