መደበኛ ያልሆነ

ሚያዝያ 2፣ 2012 ዓ.ም

ተጠርጣሪዎቹ በሰረቋት ብስክሌት አማካኝነት በቁጥጥር ስር ዋሉ

የአዲስ አበባ ፖሊስ ኮሚሽን እንዳስታወቀዉ ፤ ተጠርጣሪዎቹ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙት በቦሌ ክ/ከተማ ወረዳ 01 ልዩ ቦታው 66 ቀጠና ተብሎ ከሚጠራው አካባቢ ነው፡፡

ግለሰቦቹ መጋቢት 22 እና 26 ቀን 2012 ዓ.ም ከተለያዩ መኖሪያ ቤትና ግቢ ውስጥ በሌሊቱ ክፍለ ጊዜ ጨለማን ተገን በማድረግ ባለ 65 እና ባለ 32 ኢንቺ ሳምሰንግ ቴሌቪዥን ከነሪሲቨሮቻቸው፣ 01 ፕለይስቴሽን ፣ 02 ፎኔክስ ብስክሌት ሰርቀው ይሰወራሉ፡፡

የብስክሌቷ ባለቤት አንድ ግለሰብ ብስክሌቷን ሲያሽከርክር አግኝቶ ጉዳዩን ለፖሊስ ሪፖርት ማድረጉን ተከትሎ የስርቆት ወንጀሉን የፈፀሙ አራቱ ተጠርጣሪዎች ተይዘዋል።

ብስክሌቷን ሲያሽከረክር የተገኘው ግለሰብ ከተጠርጣሪዎቹ ላይ በቅናሽ ዋጋ መግዛቱን በምርመራ መረጋገጡን የአየር መንገድ አካባቢ ፖሊስ ጣቢያ የወንጀል እና ትራፊክ አደጋ ምርመራ ማስተባበርያ ሀላፊ ም/ኢ/ር ተስፋዬ እሸቴ ገልፀዋል፡፡

ተጠርጣሪዎቹ በፖሊስ ክትትል ተደርጎባቸው በህግ ቁጥጥር ስር የዋሉ ሲሆን ፖሊስ አስፈላጊውን መረጃ በማሰባሰብ በህግ አግባብ እንዲጠየቁ እየሰራ መሆኑን ም/ኢ/ር/ ተስፋዬ እሸቴ ተናግረዋል፡፡

የተሰረቀን ዕቃ መግዛት የህግ ተጠያቂነት የሚያስከትል እንደሆነ ኃላፊው አስታውሰው ሰዎች ዕቃ ሲገዙ ህጋዊነቱን ሊያረጋግጡ ይገባል ሲሉ በመልዕክታቸው አስገንዝበዋል፡፡

Leave a Reply

Your email address will not be published. Required fields are marked *